جَمِّلْ أَحْوَالَنَا وَ ارْحَمْ وَ لَاتَمْتَحِنَّا
Beautify Our Condition, Have Mercy on Us, and Do Not Test Us
Am
Am
الله الله يَا الله الله الله يَا الله
جَمِّلْ أَحْوَالَنَا وَارْحَمْ وَلَاتَمْتَحِنَّا
አላህ አላህ ያ አላህ፤ አላህ አላህ ያ አላህ
ሁኔታችንን አሳምርልን፣ እዘንልን፣ አትፈትነንም
يَا أَكْحَلَ العَيْنْ حَيِّ الدَّانْ لَيْلَةْ سَمَرْنَا
نَكِّشِ الدَّانْ مِنْ مَغْنَى سُلَيْمَا أَلِفْ مَعْنَى
አንተ አይነ-ኩሉ ሆይ! በጨዋታችን ሌሊት ዜማውን አድስልን
ከሱለይማ መኖሪያ ቅኝት ሺህ ትርጉሞችን ግለጽ
مِنْ سَنَا البَرْقْ لِيْ لَألَأْ عَلَى طُورِ سِينَاءْ
يَوْمْ مُوسَى اقْتَبَسْ مِنُّهْ وَ نَحْنُ اصْطَلَيْنَا
በሲና ተራራ ላይ ከበራው የመብረቅ ብርሃን የተነሳ
ሙሳ እሳት ፍለጋ በሄደበት ቀን፤ እኛ በዛ እሳት ተሞቅን
مَنْ نَظَرْ مِنْهُ بَرْقَةْ صَاحْ مِنْهَا وَ أَنَّا
مَنْ سَمِعْ أَنَّةَ المَحْزُونْ تَخْشَاهْ يَفْنَى
ከእሱ ብልጭታን ያየ ሁሉ ጮኸና ቃተተ
የሀዘንተኛውን ጩኸት የሰማ ሰው በመሰጥኦ እንዳይጠፋ ፍራ
يَا الله اِرْحَمْهُ وَانْظُرْ لُهْ فَإِنُّهْ مُعَنَّى
مِثِلْ ذُولَاكْ لِي ذَاقُوهْ مِن قَبِلْ كُنَّا
ያ አላህ እዘንለት፣ ተመልከተውም፤ እርሱ በፍቅር ተጎድቷልና
እኛ ከመኖራችን በፊት በዚያ ፍቅር እንደቀመሱት ሰዎች
أَهِلْ حَضْرَتِهْ لِي مِنْ شُرْبِهِمْ قَدْ شَرِبْنَا
وَالَّذِي عَاصَرُونَا مَا دَرُوا إِيشْ مَعْنَا
የቅርቦቹ (የሀድራው) ሰዎች ከጠጡት መጠጥ ጠጣን
በዘመናችን የነበሩት ግን የእኛን ትርጉም አላወቁም
مِن شَرَابِ المَحَبَّةْ وَ الصَّفَا لِي شَرِبْنَا
وَاصْطَبَحْنَا مِنْ أَقْدَاحِ الهَوَى وَاغْتَبَقْنَا
ከፍቅርና ከጥራት መጠጥ ጠጣን
ከፍቅር ጽዋዎች የጥዋትና የማታ መጠጥን ተጎነጨን
كُلُّ مَنْ كَانْ يُنْكِرْ ذَا يَجِي يَسْتَمِعْنَا
يَسْتَمِعْ فَضْلَنَا نَصَّ الكِتَابِ المُبِينَا
ይህን የሚያስተባብል ሁሉ ይምጣና ይስማን
ክብራችንን ይስማ፤ እርሱ የግልጹ መጽሐፍ ቃል ነውና
أَهْلُ بَيْتِ النَّبِيّ أَهْلُ الوَفَا وَاليَقِينَا
هُمْ هُمْ أَهْلُ الكِسَاءْ يَا الله بِهِمْ جُدْ عَلَيْنَا
የነቢዩ ቤተሰቦች የታማኝነትና የጽኑ እምነት ባለቤቶች ናቸው
እነሱ የኪሳእ ሰዎች ናቸው፤ አላህ ሆይ በእነሱ በኩል ችሮታህን ለግሰን
هُمْ هُمْ أَهْلُ الكِسَاءْ يَا الله بِهِمْ جُدْ عَلَيْنَا
بالعَوَافِي فِي الدَّارَيْنْ وَالكُلُّ مِنَّا
እነሱ የኪሳእ ሰዎች ናቸው፤ አላህ ሆይ በእነሱ በኩል ችሮታህን ለግሰን
በሁለቱም ዓለም ደህንነትን፤ ለእኛም ለወዳጆቻችንም ሁሉ
جَمِّل أَحْوالَنَا وَ ارْحَمْ وَ لَاتَمْتَحِنَّا
وَ الصَّلَاةُ عَلَى احْمَدْ مَاَ غَفَتْ كُلُّ عَيْنَا
ሁኔታችንን አሳምርልን፣ እዘንልን፣ አትፈትነንም
አይን እንቅልፍን በጣጣለች ቁጥር ሰለዋት በአሕመድ ላይ ይሁን