مَا مَعِي وَجَهْ قَابِل بِهْ سِوَى حُسُنْ ظَنِّي
በአንተ ላይ ካለኝ በጎ ተስፋ በቀር አንተን የምገጥምበት ፊት የለኝም::
Am
مَا مَعِي وَجَهْ قَابِل بِهْ سِوَى حُسُنْ ظَنِّي
فِيكْ يَا رَبِّ فَارْحَمْنِي وَلَا تَمْتَحِنِّي
ባንተ ካለኝ መልካም ተስፋ በቀር አንተን የምገጥምበት ፊት የለኝም
ጌታዬ ሆይ! እዘንልኝ፣ አትፈትነኝም
تُبْتْ يَا رَبِّ فَاقْبَلْ تَوْبَتِي وَاعْفُ عَنِّي
وَامْحُ ذَنْبِي وَسَامِحْ كُلَّ تَقْصِيرْ مِنِّي
ጌታዬ ሆይ! ተመልሻለሁና ተውባዬን ተቀበለኝ፣ ይቅርም በለኝ
ኃጢአቴን አብስልኝ፣ ጉድለቶቼንም ሁሉ ይቅር በለኝ
خِفِتْ مِنْ عَاقِبَةْ أَمْرِي فَجُدْ لِي بِأَمْنِي
مَحِضْ فَضْلٍ وَإِحْسَانٍ وَجُودٍ وَمَنِّ
ከነገሬ መጨረሻ ፈርቻለሁና በሰላምህ ለግሰኝ
በንፁህ ችሮታህ፣ በበጎነትህ፣ በልግስናህና በውለታህ
آه مِنْ عَثْرَتِي يَا رَبِّ مِنْهَا أَقِلْنِي
زَادْ ذَنْبِي وَمِنْ كُثْرِ الْخَطَا حَارْ ذِهْنِي
ወዮ! ከስህተቴ ጌታዬ ሆይ! አንሳኝ
ኃጢአቴ በዛ፣ ከጥፋቴ ብዛትም አእምሮዬ ተረበሸ
أَدْرِكْ أَدْرِكْ بِتَعْجِيلِ الْفَرَجْ وَانْتَقِدْنِي
وَاعْطِنِي عِلِمْ مِنْكَ يَا إِلَهِي لَدُنِّي
ድረሥልኝ፣ ድረሥልኝ፣ እፎይታን አቅርብልኝና ታደገኝ
አምላኬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ የሆነን የለዱኒ እውቀት ስጠኝ
يَنْجَلِي بِهْ عَنِ الْقَلْبِ الْصَّدِى كُلَّ رَيْنِ
ياَ سَمِيعَ الْدُّعَاءْ سَلْكَ اسْتَجِبْ وَاسْتَمِعْنِي
በሱም ከልብ ላይ ዝገትና መጋረጃ ሁሉ ይገፈፋል
ፀሎትን ሰሚ ሆይ! መልስልኝ፣ ስማኝም
مَا لِي إِلَّا أَنْتَ مُعْطِي
مَا لِي إِلَّا أَنْتَ مُغْنِي
ከአንተ በቀር ሰጪ የለኝም
ከአንተ በቀር አብቃቂ የለኝም