بَحِبَّك وَ بَرِيْدَك
እወድሃለሁ እናፍቅሃለሁ
Am
بَحِبَّك وَ بَرِيْدَك
وَاتْمَنَّى أَبُوس إِيدَك
እወድሃለሁ እናፍቅሃለሁም
የተቀደሰ እጅህን ለመሳም እመኛለሁ
خَدَّامَك وَمُرِيدَك
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
አገልጋይህና ተከታይህ ነኝ
የሀሰነይን አያት ሆይ
حَبِيْبِي مُحَمَّد
مَفِيشْ زَيُّه اتْنِين
ውዴ ሙሐመድ
እንደርሱ ያለ አንድም የለም
حُبُّه سَاكِن قَلْبِي
يَزِيد كُلِّ اتْنَيْنِ
ፍቅሩ በልቤ ውስጥ ሰፍሯል
በየቅጽበቱም ይጨምራል
جَمَالُه وَ دَلَالُه
مِتْغَطِي بْجَلَالُه
ውበቱና ርኅራኄው
በግርማ ሞገሱ ተሸፍኗል
وَتِقْعُد قْبَالُه
تُشُوفْهُم الِاتْنَيْن
በፊቱ ስትቀመጥ
ሁለቱንም በአንድነት ታያለህ
بَحِبَّك وَ بَرِيْدَك
وَاتْمَنَّى أَبُوس إِيدَك
እወድሃለሁ እናፍቅሃለሁም
የተቀደሰ እጅህን ለመሳም እመኛለሁ
خَدَّامَك وَمُرِيدَك
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
አገልጋይህና ተከታይህ ነኝ
የሀሰነይን አያት ሆይ
يَا أَجْمَل هَدِيَّة
مِنْ رَبِّ الْبَرِيَّة
አንተ ውብ ስጦታ ሆይ
ከፍጥረታት ጌታ ዘንድ የተሰጠህ
لِكُلِّ الدُّنْيَا دِيَّا
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
ለዚህ ዓለም ሁሉ
የሀሰነይን አያት ሆይ
مَاهْوِنْتَ قَمَرْهَا
وَانْتَ اللِّي مُنَوِرْهَا
አንተ የዓለሙ ጨረቃ ነህ
የምታበራትም አንተ ነህ
وَمْفَتَاح اسَرَارْهَا
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
የምስጢሮቿም መክፈቻ
የሀሰነይን አያት ሆይ
بَحِبَّك وَ بَرِيْدَك
وَاتْمَنَّى أَبُوس إِيدَك
እወድሃለሁ እናፍቅሃለሁም
የተቀደሰ እጅህን ለመሳም እመኛለሁ
خَدَّامَك وَمُرِيدَك
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
አገልጋይህና ተከታይህ ነኝ
የሀሰነይን አያት ሆይ
حَبِيبِي وَعْنَيَّا
أَحْمَد ضَيّ عْنَيَّا
ውዴና የዓይኔ ማረፊያ
አሕመድ የዓይኔ ብርሃን ነው
أَنْتَ الْغَالِي عَلَيَّا
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነህ
የሀሰነይን አያት ሆይ
وَبِنْتَك الْبَتُول
يَا عُيُونَ الرَّسُول
ንጽህት ልጅህም
የመልእክተኛው የዓይን ማረፊያ ሆይ
نَرْجُو مِنْكُم قَبُول
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
ከእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን እንከጅላለን
የሀሰነይን አያት ሆይ
بَحِبَّك وَ بَرِيْدَك
وَاتْمَنَّى أَبُوس إِيدَك
እወድሃለሁ እናፍቅሃለሁም
የተቀደሰ እጅህን ለመሳም እመኛለሁ
خَدَّامَك وَمُرِيدَك
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
አገልጋይህና ተከታይህ ነኝ
የሀሰነይን አያት ሆይ
شُوفْتُه أَنِي قُصَادِي
اتْكَسَفْت أَنَادِي
በፊቴ ባየሁት ጊዜ
ለመጥራት ሀፍረት ያዘኝ
وِبْقَلْبِي سُهَادِي يَا جَدِّي
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
ልቤ በናፍቆት ሲናወጥ
አያቴ ሆይ የሀሰነይን አያት
يِنْدَهْلِي وَاجِيلُه
يِفْرِشْلِي مَنْدِيلُه
ይጠራኛል እኔም እመጣለሁ
መጎናጸፊያውን ይዘረጋልኛል
حَبِيبِي أَنَادِيلُه
يَا جَدَّ الْحَسَنَيْن
ውዴ ሆይ ብዬ እጠራዋለሁ
የሀሰነይን አያት ሆይ