صَفَتِ النَّظْرَهْ
እይታው ጠራ
Am
Am
صَفَتِ النَّظْرَهْ طَابَتِ الْحَضْرَةْ
جَاءَتِ الْبُشْرَى لِأَهْل اللهِ
እይታው ጠራ፣ ጉባኤው ጣፈጠ
የምስራች መጣ ለአላህ ወዳጆች
قَامُوْا سُكَارَى لِذِي الْبِشَارَه
جَعْلَوْا عِمَارَهْ شُكْراً لِلّهِ
እንደ ሰካራሞች ቆሙ ለዚያ ብስራት
አላህን ለማመስገን ዒማራውን አደመቁ
أَيُّهَا الْحَاضِرْ اُذْكُرْ وَذَاكِرْ
إِيَّاكَ تُنْكِرْ حَالَ أَهْلِ اللهِ
አንተ ተገኝ የሆንክ ሆይ! አውሳ አሳውስም
የአላህ ወዳጆችን ሁኔታ ከመካድ ተጠንቀቅ
فَسَلِّمْ لَهُمْ فِيمَا عَرَاهُمْ
وَاعْلَمْ أَنَّهُمْ غَابُوْا فِي اللهِ
ለገጠማቸው መንፈሳዊ ሁኔታ እጅ ስጥላቸው
በእርግጥም እነርሱ በአላህ ውስጥ መጥፋታቸውን እወቅ
فَالْوَجْدُ بِهِمْ دَاعِيْ يَدْعِيْهِمْ
يَطْرَأْ عَلَيْهِمْ فِيْ ذِكْرِ اللهِ
ወጅድ ጠሪ ሆኖ ይጠራቸዋልና
በአላህ ዚክር ውስጥ በድንገት ይመጣባቸዋል
وَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَلْيَتَوَاجَدْ
قَصْداً يَتَعَرَّضْ لِفَضْلِ اللهِ
ወጅድ ያላገኘ ይሻው (ሊያመጣው ይጣጣር)
የአላህን ችሮታ ፈልጎ ራሱን ያጋልጥ
هَكَذَا قَالُوْا وَلِذَا مَالَوْا
وَلَقَدْ غَالُوْا فِي ذِكْرِ اللهِ
እንዲህ አሉ፣ ለዚህም ወዘወዙ
በአላህም ዚክር ውስጥ ድንበር እስከሚጥሉ ገቡ
حَتَّى قَدْ ظَنَّا مَنْ لَيْسَ مِنَّا
أَنَّا جُنِنَّا بِذِكْرِاللهِ
ከእኛ ያልሆኑት እስኪያምኑ ድረስ
በአላህ ዚክር ምክኒያት አብደናል ብለው
هَنِيْئاً لَنَا ثُمَّ بُشْرَانَا
إِنْ كَانَ لَنَا حُمْقٌ فِي اللهِ
መልካም ዕድል ለእኛ፣ ደግሞም ብስራት ይሁንልን
"እብደታችን" በአላህ ፍቅር ከሆነ