أَلْفٍ صَلَّى الله عَلَى زَيْنِ الْوُجُودْ
ሺህ የአላህ ሰላት በዓለሙ ጌጥ ላይ ይሁን።
Am
أَلْفٍ صَلَّى الله عَلَى زَيْنِ الْوُجُودْ
مَنْ سَكَنْ طَيْبَة وَخَيَّمْ في زَرُودْ
የአላህ ሺህ ሰላም በህልውና ጌጥ ላይ ይሁን
በጣይባ በኖረውና በዘሩድ በሰፈረው
يَا بُدُورَ الْحَيِّ يَا رَبْعَ الْكِرَامْ
بَلِّغُو ظَبْيَ الْحِمَى مِنِّي السَّلَامْ
የሰፈሩ ሙሉ ጨረቃዎች ሆይ የደጋጎች ማረፊያ
ለጥበቃው ስፍራ ሜዳ ፍየል ሰላምታዬን አድርሱልኝ
إِنْ تَهَتَكْنَا عَلَيْكُمْ لَا نُلَامْ
غَلَبَ الْوَجْدُ عَلَيْنَا وَ الْغَرَامْ
በእናንተ ፍቅር ብንጋለጥ አንወቀስም
ናፍቆትና ፍቅር አሸንፎናልና
لَا يَنَامُ اللَّيْلَ عَاشِقْ مُسْتَهَامْ
إِنَّمَا النَّومُ عَلَى الْعَاشِقْ حَرَامْ
ክፉኛ የናፈቀ አፍቃሪ ሌሊቱን አይተኛም
እንቅልፍ ለአፍቃሪ እርም ነውና
سَادَتِي إِنْ لَمْ تَحِنُّو بِاللِّقَا
مِتُّ وَجْدًا فَلَكُمْ طُولُ الْبَقَاء
ጌቶቼ ሆይ በመገናኘት ካልራራችሁልኝ
በናፍቆት እሞታለሁ፤ ለእናንተ ግን ረጅም ዕድሜ ይሁን
أَنَا إِنْ لَمْ أَهْوَا غِزْلَانَ النَّقَاء
أَيُّ فَرْقٍ بَيْنَ قَلْبِي وَ الْجَمَادْ
እኔ የነቃን ሜዳ ፍየሎች ካልወደድኩ
በልቤና በግዑዝ ድንጋይ መካከል ምን ልዩነት አለ?
آنَسَ اللهُ بِكُمْ أَوْقَاتَنَا
وَسَقَى وَادِيكُمُ فَيْضَ الْغَمَامْ
አላህ በእናንተ ጊዜያችንን ያጣፍጥልን
ሸለቆአችሁንም በደመና ዝናብ ያርጥብላችሁ