أَيَا مُرِيْدَ الله
Am
الله الله الله الله سَيَّدِي الله
الله الله الله اَلْعَظِيْمُ الله
አላህ አላህ አላህ አላህ ጌታዬ አላህ
አላህ አላህ አላህ ታላቁ አላህ
أَيَا مُرِيْدَ اللهُ نُعِيدْ لَكْ قَوْلِ اصْغَهْ
إِذَا تَفْهَمْ قَوْلِي بِهِ تَصِلْ لِلّهْ
አንተ የአላህ ፈላጊ ሆይ! ቃሌን ደግመን እንነግርሃለንና አድምጠው
ቃሌን ከተረዳህ በእርሱም ወደ አላህ ትደርሳለህ
عَلَيْكَ يَا مُرِيدْ بِخَمْرَةِ التَّوْحِيدُه
وَإِنْ تَبْغِ الْمَزِيدْ فَالْغَيْرُ عَنْكَ انْسَهْ
አንተ ፈላጊ ሆይ! በተውሂድ ወይን አደራህን
ተጨማሪም ከፈለግህ ከእርሱ ውጭ ያለውን ሁሉ እርሳ
فَاذْكُرْ الاسْمَ الْأَعْظَمْ وَاطْوِ الْكَوْنَ تَغْنَمْ
وَخُضْ بَحْرَ الْقِدَمْ فَذَاكَ بَحْرُ الله
ታላቁን ስም አውሳ፤ አጽናፈ ዓለሙንም ጥቅለልና ትርፍን አግኝ
የጥንታዊነትን ባሕርም ጥለቅ፤ ያ የአላህ ባሕር ነውና
وَخُضْ بَحْرَ الْأَنْوَارْ وَالْمَعْنَى وَالْأَسَرَارْ
وَافْنِ هَذِي الدِّيَارْ يَبْلُغْ قَلْبُكْ مُنَاهْ
የብርሃናትን፣ የትርጉማትንና የምስጢራትን ባሕር ጥለቅ
እነዚህን መኖሪያዎች አጥፋ፤ ልብህም ምኞቱን ይደርሳል
وَلْتَفْنَ في الْمَعْبُودْ تَذُوقْ مَعْنَى الشُّهُودُ
إِذْ لَيْسَ ذَا الْوُجُودْ إِلَّا مِنْ نُورِ الله
በተመለኪው ውስጥ ጥፋ፤ የምስክርነትንም ጣዕም ቅመስ
ይህ ህልውና ከአላህ ብርሃን በቀር ሌላ አይደለምና
الْمُلْكُ وَالْمَلَكُوتْ كَذَاكَ الْجَبَرُوتْ
فَكُلُهَا نُعُوتْ وَالذَّاتُ مُسَمَّاهُ
የሙልክ፣ የመለኩት እንዲሁም የጀበሩት ዓለማት
ሁሉም መገለጫዎች ናቸው፤ ዛቱ ግን ተሰያሚው ነው
فَغِبْ عَنِ الصِّفَاتْ وَافْنَ في ذَاتِ الذَّاتْ
هَذِي تَلَوُّنَاتْ مَصِيرُهَا لِلِهُ
ከባሕርያቱ ተሰወርና በዛቱ ውስጥ ቅለጥ
እነዚህ ሁሉ መገለጫዎች ናቸው፤ መመለሻቸውም ወደ አላህ ነው
إِلَيْهِ الْمُنْتَهَى وَمِنْهُ الْمُبْتَدَا
وَالْآنَ قَدْ بَدَا وَالْكَوْنُ فِي حُلَاهْ
ፍጻሜው ወደ እርሱ ነው፤ መጀመሪያውም ከእርሱ ነው
አሁን ግን ተገለጠ፤ ዓለሙም በእርሱ ውበት ደመቀ
لَهُ الْكَوْنُ مِرْآتْ وَمَظْهَرُ الصِّفَاتْ
مُحَمَّدْ نُورُ الذَّاتْ عَلَيْهِ صَلَّى الله
ለእርሱ ዓለሙ መስታወትና የባሕርያቱ መገለጫ ነው
ሙሐመድ የዛቱ ብርሃን ናቸው፤ የአላህ ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን
الْعَلَاوِيْ يَقُوْلْ قَوْلًا مِنْهُ مَقْبُولُ
تَهِيْمُ بِهِ الْعُقُولْ تَغِيبْ فِي ذَاتِ الله
አል-ዐላዊ ተቀባይነት ያለው ንግግርን ይናገራል
አዕምሮዎች በእርሱ ይደመማሉ፤ በአላህ ዛት ውስጥም ይሰወራሉ