مِنْ جَمَالِ الْكَوْنِ خَمْرِي
ወይኔ ከዓለም ውበት ነው
Am
Am
مِنْ جَمَالِ الْكَوْنِ خَمْرِي
ذَقْتُهُ صِرْفاً حَلَالَا
ከዓለሙ ውበት የመጣ ነው ወይኔ
ያለ አንዳች ቅልቅል ቀመስኩት በክብር በእውኔ
وَهْوَ مِنْ أَوْصَافِ بَدْرِي
قَدْحَوَى ذَاكَ الْجَمَالَا
እርሱ ከጨረቃዬ ባሕርያት የተቀዳ ነው
ያንንም ሙሉ ውበት አጠቃሎ የያዘ ነው
وَجْهٌ قَدْ لَاحَ سَنَاهْ
وَالْكَوْنُ غَدَا مِرْآهْ
ብርሃኑ ደምቆ የበራለት ፊት
ዓለሙም ሆነለት የመመልከቻ መስታወት
إِنْ رُمْتَ فُؤَادِي لِقَاهْ
فَاجْعَلْ هَوَاكَ هَوَاهْ
ልቤ ሆይ እርሱን መገናኘት ከሻትህ
ፍላጎትህን ከእርሱ ፍላጎት ጋር አስማማህ
أَنَا بِالْرُّوْحِ سَمَاءُ
أَنَا بِالْجِسْمِ هَبَاءُ
እኔ በመንፈሴ ሰፊ ሰማይ ነኝ
በአካሌ ግን ኢምንት አቧራ ነኝ
أَنَا زَهْرٌ أَنَا مَاءُ
تِهْتُ مِنْ وَجْدِي دَلَالَا
እኔ አበባ ነኝ እኔም ውሃ ነኝ
በውዴታዬ ጣፋጭነት ውስጥ ጠፍቻለሁኝ
وَالْرُّوْحُ رَقَى مَرْقَاهْ
وَالْقَلْبُ غَدَا يَرْعَاهْ
መንፈስ ወደ ላቀ ማዕረጓ ወጣች
ልብም ሊጠብቃትና ሊንከባከባት ተገኘች
وَالْجِسْمُ سَعَى مَسْعَاهْ
لِيَنَالَ بِذَاكَ مُنَاهْ
አካልም በመንገዷ ላይ ተቻኮለች
በዚህም የልቧን ምኞት አገኘች
يَا عَذُوْلاً لَامَ جَهْلاً
مُغْرَماً قَدْ نَالَ وَصْلَا
ባለማወቅ የምትወቅስ ወቃሽ ሆይ
ውዴታውን ያገኘን ፍቅረኛ ለምን ትወቅሳለህ ወይ
إِنْ تَلُمْ صِدْقاً سَتُبْلَى
وَتَذُوْقُ الْحُبَّ حَالاَ
በእውነት ብትወቅስ አንተም ትፈተናለህ
ያንኑ ቅጽበት የፍቅሩን ጣዕም ትቀምሳለህ
بِفَنَائِكَ عَنْ سِوَاهْ
تَأْوِيْ لِفِنَاءِ بَقَاهْ
ከእርሱ ውጪ ካሉ ነገሮች ሁሉ በመጥፋትህ
በዘላለማዊነቱ ሰፊ ጥላ ስር ትጠላለህ
وَبِبَرْدِ شَرَابِ رِضَاهْ
يُطْفِي الْفُؤَادُ جَوَاهْ
በውዴታው ቀዝቃዛ መጠጥ አማካኝነት
የልብ የቃጠሎ ናፍቆት ይረካል በጸጥታ
صَلَوَاتُ اللهِ تُهْدَى
مِنْ جَمِيْعِ الْطِّيْبِ أَنْدَى
የአላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ
ከማንኛውም ሽቶ ይልቅ እጅግ የሚውድ
لِرَسُوْلٍ قَدْ تَبَدَّى
نُوْرُهُ يَمْحُو الْضَّلَالَا
ለተገለጠው መለክተኛ ይሁን
ብርሃኑ ጥመትን የሚያጠፋ ለሆነው መሪ
بِسَلامٍ لا يَتَنَاهْ
وَالْاَلِ أُهَيْلِ الْجَاهْ
በማያልቅ ሰላምታና ክብር
ለቤተሰቦቹም ያ ከፍ ያለ ማዕረግ ላላቸው
وَالْصَّحْبِ وَمَنْ وَالَاهْ
وَجِيْعِ رِجَالِ الله
ለባልደረቦቹና ለተከተሏቸው ሁሉ
እንዲሁም ለአላህ ደጋግ ወዳጆች ሁሉ