قَصِيدَةُ الْمَقْبُولَةِ
The Accepted Poem
Am
صَلَّى اللهُ عَلَى مُحَمَّدْ
صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمْ
አላህ በሙሐመድ ላይ ሰላዋትን ያውርድ
አላህ ሰላምታና በረከትን በእርሳቸው ላይ ያውርድ
رَوْضَةُ الْهَادِي نَبِيِنَا
هُيِّئَتْ لِلْمُتَّقِينَا
የመሪያችን የነቢያችን ዐጸድ (መስጊድ)
ለአላህን ፈሪዎች ተዘጋጅታለች
كُلُّ مَنْ قَالُوا رَضِينَا
بِالْحَبِيبْ مَوْلَاىْ مُحَمَّدْ
«ወደናል» ያሉት ሁሉ
በተወዳጁ ጌታችን ሙሐመድ
حُبُّهُ عَيْنُ الْكَمَالِ
جَاهُهُ عَالٍ وَغَالِ
እርሳቸውን መውደድ የፍጽምና ምንጭ ነው
ደረጃቸው ከፍ ያለና ውድ ነው
صَحْبُهُ خَيْرُ الرِّجَالِ
بَايَعُوا الْهَادِي مُحَمَّدْ
ባልደረቦቻቸው ከሰዎች ሁሉ ምርጥ ናቸው
ለመሪው ሙሐመድ ቃል ኪዳን የገቡ
وَجْهُهُ فَاقَ الْبُدُورَا
زَادَهُ الْمَوْلَى سُرُورَا
ፊታቸው ሙሉ ጨረቃዎችን በለጠ
ጌታም በደስታ ላይ ደስታን ጨመረላቸው
قَدْ بَدَا فِي الْكَوْنِ نُورَا
قَبْلَ خَلْقِ اللَّهِ مُحَمَّدُ
በአጽናፉ ውስጥ ብርሃን ሆኖ ታየ
አላህ ፍጥረታትን ከመፍጠሩ በፊት፣ ሙሐመድ
حُبُّهُ فَرْضٌ وَحَتْمُ
مِدْحَهُ خَيْرٌ وَغُنْمُ
እርሳቸውን መውደድ ግዴታና እርግጥ ነው
ማወደሳቸው በጎነትና ትርፍ ነው
لَيْسَ يَأْتِي الْقَلْبَ هَمُّ
لِلَّذِي يَهْوَي مُحَمَّدْ
ወደ ልብ ምንም ሀዘን አይመጣም
ሙሐመድን ለሚወድ ሰው
بَحْرُ عِلْمِ اللهِ أَحْمَدْ
كُلُّ مَنْ يَلْقَاهُ يَسْعَدْ
አሕመድ የአላህ እውቀት ውቅያኖስ ናቸው
የተገናኛቸው ሁሉ ደስተኛ ይሆናል
حَوْضُهُ الصَّافِي الْمُبَرَّدْ
لِلَّذِي يَعْشَقْ مُحَمَّدْ
ንጹህና ቀዝቃዛው ምንጫቸው
ሙሐመድን ላፈቀረ ሰው ነው
يَفْتَحُ اللهُ الْعَوَالِمْ
بإِمَامٍ لِلْمَكَارِمْ
አላህ ዓለማትን ይከፍታል
በክቡር ሥነ-ምግባር መሪ አማካይነት
لِجَمِيعِ الرُّسْلِ خَاتَمْ
الحَبِيبْ مَوْلَاىْ مُحَمَّدْ
ለመልክተኞች ሁሉ መደምደሚያ በሆኑት
በተወዳጁ ጌታችን ሙሐመድ
خَيْرُ خَلْقِ اللهِ طَهَ
مِثْلُ شَمْسٍ فِي ضُحَاهَا
ጧሃ የአላህ ፍጥረታት ምርጥ ናቸው
እንደ ጧት ፀሐይ ብርሃን
هَذِهِ الدُّنْيَا نَرَاهَا
فِي ضِيَاءٍ مِنْ مُحَمَّدْ
ይህችን የምናያትን ዓለም
በሙሐመድ ብርሃን ውስጥ ናት
أَكْحَلُ الْعَيْنَيْنِ أَدْعَجْ
نُورُهُ الْمَحْبُوبُ أَبْلَجْ
ዐይኖቻቸው የተኳሉና ጥቁር የሆኑ
የተወዳጁ ብርሃን ደማቅ ነው
أَشْنَبُ الْأَسْنَانِ أَفْلَجْ
فَاقَ رُسْلَ اللّهْ مُحَمَّدْ
ጥሮሳቸው የሚያበሩና ክፍተት ያላቸው
ሙሐመድ የአላህን መልክተኞች በለጡ
وَجْهُهُ يَا نَاسُ نَائِرْ
سَيِّدِي مَوْلَى الْبَشَائِرْ
ሰዎች ሆይ፣ ፊታቸው የሚያበራ ነው
ጌታዬ የብስራቶች ባለቤት
ذُخْرُنَا نُورُ الْبَصَائِرْ
إِسْمُهُ الْهَادِي مُحَمَّدْ
ስንቃችን፣ የማስተዋል ብርሃን
ስማቸው መሪው ሙሐመድ ነው
قَدْرُهُ الْعَالِي الْمُفَضَّلْ
وَصْفُهُ الْغَالِي الْمُكَمَّلْ
ደረጃቸው ከፍተኛና የተመረጠ ነው
ባህሪያቸው ውድና የተሟላ ነው
وَحْيُ رَبِّي قَدْ تَنَزَّلْ
لِلْحَبِيبْ مَوْلَاىْ مُحَمَّدْ
የጌታዬ ራዕይ ወርዷል
ለተወዳጁ ጌታችን ሙሐመድ
فَضْلُهُ عَمَّ النَّوَاحِي
لِظَلَامِ الْكُفْرِ مَاحِي
ችሮታቸው አቅጣጫዎችን ሁሉ አዳረሰ
የክህደትን ጨለማ አጥፊ ነው
فِي الصَّحَارِى وَالْبِطَاحِ
أَشْرَقَتْ أَنْوَارْ مُحَمَّدْ
በበረሃዎችና በሜዳዎች ላይ
የሙሐመድ ብርሃናት አበሩ
شَرْعُهُ لِلْكَوْنِ يَعْمُرْ
وَبِهِ الْأَيَّامُ تَفْخَرْ
ሕጋቸው አጽናፉን ያለማል
ቀናቶችም በእርሳቸው ይኮራሉ
دَمْعُ مَنْ يَهْوَاهُ يَقْطُرْ
مِنْ غَرَامٍ فِي مُحَمَّدْ
የአፍቃሪዎቻቸው እንባ ይንጠባጠባል
ለሙሐመድ ካላቸው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ
حُسْنُهُ لِلْبَدْرِ أَخْجَلْ
وَبِهِ غَيْبٌ تَنَزَّلْ
ውበታቸው ሙሉ ጨረቃን አሳፈረ
በእርሳቸውም ሩቅ ምስጢር ወረደ
وَجُمُوعَ الْكُفْرِ عُطِّلْ
مِنْ عَزِيمِ مَوْلَانَا مُحَمَّدْ
የክህደት ሠራዊትም ተጨናገፉ
በጌታችን ሙሐመድ ቆራጥነት
الْبَعِيرُ يَشْكُو الْمَجَاعَهْ
لِلنَّبِيِّ بَيْنَ الْجَمَاعَةْ
ግመሉ ረሀቡን አቤት አለ
በሕዝቡ መካከል ለነብዩ
قَالَ يَا مَوْلَى الشَّفَاعَةْ
كُنْ شَفِيعِي يَا مُحَمَّدْ
አለ፡- «የምልጃ ባለቤት ሆይ
አማላጄ ይሁኑኝ፣ ኦ ሙሐመድ»
نَادَتِ الْهَادِي غَزَالَهْ
تَشْتَكِي تُبْدِي مَقَالَهْ
ሚዳቋም መሪውን ተጣራች
ቅሬታዋን እያሰማች ቃሏን ገለጸች
يَا إِمَامًا لِلْرِّسَالَهْ
كُنْ ضَمِينِي يَا مُحَمَّدْ
«የመልዕክቱ መሪ ሆይ
ዋሴ ይሁኑኝ፣ ኦ ሙሐመድ»
هَذِهِ الدُّنْيَا كَسَاعَهْ
إِجْعَلِ الْأَعْمَالَ طَاعَهْ
ይህች ዓለም እንደ አንዲት ሰዓት ናት
ስራዎችን ሁሉ ታዛዥነት አድርግ
وَاشْتَرِي خَيْرَ بِضَاعَهْ
زَوْرَةَ الْهَادِي مُحَمَّدْ
ምርጥ የሆነውን ሸቀጥም ግዛ
የመሪውን ሙሐመድን ጉብኝት
هَذِهِ الدُّنْيَا تَزُولُ
وَالْبَقَا لَيْسَ يَطُولُ
ይህች ዓለም ጠፊ ናት
ቆይታዋም አይረዝምም
أَيْنَ مَنْ يَمْشِي يَقُولُ
كُنْ شَفِيعِي يَا مُحَمَّدْ
እየተራመደ እንዲህ የሚለው የት አለ
«አማላጄ ይሁኑኝ፣ ኦ ሙሐመድ»
رَبَّنَا يَسِّرْ وَسَهِّلْ
زَوْرَةَ الْمُخْتَارِ عَجِّلْ
ጌታችን ሆይ! አግራልንና ቀለል አድርግልን
የተመረጡትን ጉብኝት አፍጥንልን
دَمْعُنَا يَهْمِى وَيَنْزِلْ
مِنْ غَرَامٍ فِي مُحَمَّدْ
እንባችን ይፈሳል ይወርዳል
ለሙሐመድ ካለን ጥልቅ ፍቅር
رَبَّنَا هَيِّئْ طَرِيقَا
كُنْ لَنَا رَبِّي رَفِيقَا
ጌታችን ሆይ! መንገዱን አዘጋጅልን
ጌታዬ ሆይ፣ ጓደኛ ሁነን
كَيْ نَرَى بَدْرًا شَفِيقَا
الْحَبِيبْ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
አዛኙን ሙሉ ጨረቃ እንድናይ
ተወዳጁን ጌታዬን ሙሐመድን
ظَنُّنَا فِيكَ جَمِيلُ
أَنْتَ يَا رَبِّي وَكِيلُ
በአንተ ላይ ያለን ተስፋ ያማረ ነው
ጌታዬ ሆይ፣ አንተ መጠጊያችን ነህ
وَالنَّبِي نِعْمَ الْكَفِيلُ
الْحَبِيبْ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ነብዩም ምንኛ ያማሩ ዋስ ናቸው
ተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
كُلُّنَا يَرْجُو الْبَشَارَهْ
بِالرَّحِيلْ نَحْوَ الزِّيَارَهْ
ሁላችንም ብስራቱን እንመኛለን
ወደ ጉብኝቱ ለመጓዝ
حَبَّذَا تِلْكَ التِّجَارَهْ
زَوْرَةُ الْهَادِي مُحَمَّدْ
ያ ንግድ ምንኛ ያማረ ነው
የመሪውን የሙሐመድን ጉብኝት
أَيْنَ أَصْحَابُ الكَمَالِ
أَيْنَ سَادَاتُ الرِّجَالِ
የፍጽምና ባለቤቶች የት አሉ
የሰዎች አለቆችስ የት አሉ
أَنْفَقُوا مِنْ خَيْرِ مَالِ
قَاصِدِينَ مَوْلَاىْ مُحَمَّدْ
ከምርጥ ሀብታቸው ለገሱ
ጌታዬን ሙሐመድን አስበው
دَمْعُهُمْ يَقْطُرْ وَبَادِي
كُلَّمَا حَلُّوا بِوَادِي
እንባቸው ይንጠባጠባል፣ ይታያልም
ሸለቆ ውስጥ በሰፈሩ ቁጥር
قَصْدُهُمْ خَيْرُ العِبَادِ
الْحَبِيبْ مَوْلَاىْ مُحَمَّدْ
አላማቸው ምርጡ ባሪያ ነው
ተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
سَارَ بِالرَّحْمَنِ سَارَا
رَكْبُهُمْ يَطْوِي الْقِفَارَا
በአዛኙ ጌታ ተጓዙ
ቅፍለታቸው በረሃዎችን ያቋርጣል
وَرَأَيْنَاهُمْ جَهَارَا
عَاشِقِينْ مَوْلَاىْ مُحَمَّدْ
በግልጽም አየናቸው
ጌታዬን ሙሐመድን የሚያፈቅሩ ሆነው
حَرُّ هَاتِيْكَ الْبَوَادِي
مِثْلُ ثَلْجٍ مِنْ وِدَادِ
የዚያ በረሃ ሙቀት
ከፍቅር የተነሳ እንደ በረዶ ነው
حِصْنُهُمْ خَيْرُ الْعِبَادِ
رَحْمَةُ الْهَادِي مُحَمَّدْ
ምሽጋቸው ምርጡ የአላህ ባሪያ ነው
የመሪው የሙሐመድ እዝነት
اسْكُبِ الدَّمْعَ حَلَالًا
عِنْدَمَا تَلْقَى الْهِلَالَا
እንባህን በነጻነት አፍስስ
ጨረቃዋን ስትመለከት
مِنْ بَعِيدٍ قَدْ تَلَالَا
فِيْهِ نُورٌ مِنْ مُحَمَّدْ
ከሩቅ በኩል ታንጸባርቃለች
በውስጧ ከሙሐመድ የሆነ ብርሃን አለ
هَذِهِ الْخَضْرَاءُ تَظْهَرْ
نُورُهَا لِلْعَقْلِ يَبْهَرْ
ይህች አረንጓዴዋ ጉልላት ትታያለች
ብርሃኗ አእምሮን ያንፀባርቃል
عِنْدَ رُؤْيَاهَا تَحَدَّرْ
دَمْعُ مَنْ يَعْشَقُ مُحَمَّدْ
እርሷን ሲያይ ይወርዳል
ሙሐመድን የሚያፈቅር ሰው እንባ
رَوْضَةُ الْهَادِي نَبِيِّنَا
تُفْرِحُ الْقَلْبَ الْحَزِينَا
የመሪያችን የነብያችን ዐጸድ
አዘንተኛውን ልብ ታስደስታለች
أَبْشِرُوا يَا زَائِرِينَا
بِالشَّفَاعَةِ مِنْ مُحَمَّدْ
ጎብኚዎቻችን ሆይ ደስ ይበላችሁ
ከሙሐመድ በሆነው ምልጃ
هَذِهِ الرَّوْضَةُ أَبْشِرْ
قَدْ وَصَلْنَا لِلْمُبَشِّرْ
ይህች ዐጸድ ናት፣ ደስ ይበልህ
ወደ አብሳሪው ደርሰናል
أَمْرُ دُنْيَا لَا تُفَكِّرْ
وَانْظُرِ الْهَادِي مُحَمَّدْ
ስለ ዓለማዊ ጉዳይ አታስብ
መሪውን ሙሐመድን ተመልከት
كُلُّ مَنْ زَارَ الْمَقَامَا
فَالنَّبِي رَدَّ السَّلَامَا
ቦታቸውን የጎበኘ ሁሉ
ነብዩ ሰላምታ ይመልሱለታል
يَعْرِفُ الْخَلْقَ تَمَامَا
بَشِّرُوا زُوَّارَ مُحَمَّدْ
ፍጥረታትን በሚገባ ያውቃሉ
ለሙሐመድ ጎብኚዎች አብስሩ
هَامَتْ الْأَرْوَاحُ حُبًّا
دَمْعُنَا قَدْ سَالَ صَبًّا
ነፍሳት በፍቅር ተቅበዘበዙ
እንባችንም እንደ ጅረት ፈሰሰ
نَالَتْ الزُّوَّارُ قُرْبًا
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ጎብኚዎችም ቅርበትን አገኙ
ከተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ ጋር
يَا حَبِيبَ الْمُتَّقِينَا
وَسِرَاجًا وَمُبِينَا
የአላህን ፈሪዎች ተወዳጅ ሆይ
አብሪ መብራትና ግልጽ የሆናችሁ
يَا أَبَا الْقَاسِمْ دُعِينَا
فَأَتَيْنَا يَا مُحَمَّدْ
አቡል ቃሲም ሆይ፣ ተጠርተናል
መጥተናልም፣ ኦ ሙሐመድ
مَرْحَبًا يَا مُصْطَفَانَا
حُبُّكَ الْغَالِي أَتَانَا
እንኳን ደህና መጡ፣ የተመረጡት መሪያችን
ክቡር ፍቅርዎ መጥቶልናል
مِنْ بَعِيدٍ قَدْ دَعَانَا
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ከሩቅ ቦታም ጠርቶናል
ወደ ተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
كَيْ نَرَي ذَاكَ الْمَقَامَا
فِيهِ بَدْرٌ قَدْ تَسَامَى
ያንን ቦታ እንድናይ
ከፍ ያለ ሙሉ ጨረቃ ያለበትን
وَأَخُو الشَّوْقِ تَسَامِي
مِنْ هِيَامٍ فِي مُحَمَّدْ
የናፍቆት ባለቤትም ከፍ አለ
ለሙሐመድ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ
يَا شَفِيعًا لِلذُّنُوبِ
وَغِيَاثًا فِي الْكُرُوبِ
ለኃጢአቶች አማላጅ የሆኑ ሆይ
በጭንቀቶችም ጊዜ ታዳጊ
وَضِيَاءً لِلْقُلُوبِ
أَنْتَ نُورُ يَا مُحَمَّدْ
ለልቦችም ብርሃን የሆኑ
እርሶ ብርሃን ነዎት፣ ኦ ሙሐመድ
جَاهُكَ الْمَرْجُو عَظِيمٌ
أَنْتَ مِفْضَالٌ كَرِيمٌ
የሚከጀለው ደረጃዎ ታላቅ ነው
እርሶ ቸርና ለጋስ ነዎት
وَرَءُوفٌ وَرَحِيمٌ
وَعَفُوٌّ يَا مُحَمَّدْ
አዛኝና ሩህሩህ ነዎት
ይቅር ባይም ነዎት፣ ኦ ሙሐመድ
أَبْشِرُوا يَا مَنْ رَأَيْتُمْ
رَوْضَةَ الْهَادِي وَزُرْتُمْ
ደስ ይበላችሁ እናንተ ያያችሁ
የመሪውን ዐጸድ የጎበኛችሁ
عِنْدَ رَبِّ الْعَرْشِ كُنْتُمْ
زَائِرِينَ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
በዐርሹ ጌታ ዘንድ ሆናችሁ
ጌታዬን ሙሐመድን ጎብኚዎች ናችሁ
قَدَّرَ الْمَوْلَى السَّعَادَهْ
وَدَعَاكُمْ لِلْعِبَادَهْ
ጌታ ደስታን ወሰነላችሁ
ወደ አምልኮም ጠራችሁ
هَذِهِ الْحُسْنَى زِيَادَهْ
زَوْرَةُ الْهَادِي مُحَمَّدْ
ይህችም ተጨማሪ የመጨረሻይቱ መልካም ነገር ናት
የመሪው የሙሐመድ ጉብኝት
سَعْدُكُمْ يَا مَنْ تَزُورُوا
وَجْهُكُمْ يَعْلُوهُ نُورُ
እናንተ የምትጎበኙት ደስታችሁ!
ፊታችሁን ብርሃን ይሸፍነዋል
رَبُّكُمْ رَبٌّ غَفُورُ
لِلَّذِي قَدْ زَارَ مُحَمَّدْ
ጌታችሁ እጅግ መሐሪ ጌታ ነው
ሙሐመድን ለጎበኘ ሰው
لَوْ رَأَيْنَا الْوَاقِفِينَا
لَوْ رَأَيْنَا الْقَاعِدِينَا
የቆሙትን ሰዎች ባየን ኖሮ
የተቀመጡትንም ባየን ኖሮ
لَوْ رَأَيْنَا السَّائِلِينَا
الشَّفَاعَةَ مِنْ مُحَمَّدْ
የሚለምኑትን ባየን ኖሮ
ምልጃን ከሙሐመድ
نُورُ خَيْرِ الْخَلْقِ يُجْلِي
وَكِتَابُ اللهِ يُتْلِي
የምርጥ ፍጡር ብርሃን ግልጽ ያደርጋል
የአላህም መጽሐፍ ይነበባል
وَعُلُومُ الشَّرْعِ تُمْلِي
عِنْدَ مَوْلَايْ مُحَمَّد
የሸሪዓ እውቀቶችም ይነገራሉ
በጌታዬ ሙሐመድ ዘንድ
إِنْ رَجَعْتُمْ بِالسَّلَامَةْ
أَخْبِرُوا أَهْلَ الْمَلَامَةْ
በሰላም ከተመለሳችሁ
ለወቃሾቹ ሰዎች ንገሯቸው
كَيْ يَجِيئُوا مِنْ تِهَامَةْ
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ከቲሃማ እንዲመጡ
ወደ ተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
عَرِّفُوهُمْ بِالْمَقَامِ
أَخْبِرُوهُمْ بِالْهِِيَامِ
የቦታውን ክብር አስታውቋቸው
ስለ ጠለቀው ፍቅር ንገሯቸው
أَيْقِظُوهُمْ مِنْ مَنَامِ
كَيْ يَزُورُوا لِمُحَمَّدْ
ከእንቅልፋቸው ቀስቅሷቸው
ሙሐመድን እንዲጎበኙ
لَوْ عَلِمْتُمْ يَا عَوَاذِلْ
مَا سَكَنْتُمْ فِي الْمَنَازِلْ
ወቃሾች ሆይ ብታውቁ ኖሮ
በቤቶቻችሁ ውስጥ ባልተቀመጣችሁ ነበር
مَا لَنَا فِي الْقَلْبِ شَاغِلْ
كُلُّنَا يَهْوَى مُحَمَّدْ
በልባችን ውስጥ ሌላ አሳሳቢ የለንም
ሁላችንም ሙሐመድን እናፈቅራለን
قَدْ سَرَيْنَا بِالْمَطَايَا
لِلنَّبِي خَيْرِ الْبَرَايَا
በአጋሰሶች በሌሊት ተጓዝን
ወደ ነብዩ፣ ከፍጥረታት ሁሉ ምርጥ ወደሆኑት
سَيِّدِي كَنْزِ الْعَطَايَا
الْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ጌታዬ፣ የስጦታዎች ክምችት
ተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
حُبُّهُ يُحْيِي الْقُلُوبَا
يَغْفِرُ اللهُ الذُّنُوبَا
እርሳቸውን መውደድ ልቦችን ህያው ያደርጋል
አላህም ኃጢአቶችን ይምራል
يَسْتُرُ اللهُ الْعُيُوبَا
بِالْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
አላህ ጉድለቶችን ይሸፍናል
በተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ ምክንያት
يَا رَسُولَ اللهِ نَادِ
أَهْلَ حُبٍّ وَوِدَادِ
የአላህ መልክተኛ ሆይ ይጠሩ
የፍቅርና የውዴታ ሰዎችን
هُمْ بِشَوْقٍ فِي بِعَادِ
أُدْعُهُمْ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
እነሱ ርቀው በናፍቆት ውስጥ ናቸው
ጌታዬ ሙሐመድ ሆይ ይጠሯቸው
وَتَوَجَّهْ لِلْمُقَدِّرْ
رَبُّنَا الْمُعْطِي يُيَسِّرْ
ወደ ወሳኙ ጌታም ፊትን አዙሩ
ሰጪው ጌታችን ያገራዋል
بَعْدَ عُسْرٍ كَيْ نُبَدِّرْ
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ከችግር በኋላ ፈጥነን እንድንጓዝ
ወደ ተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
صَلَوَاتٌ طَيِّبَاتُ
زَاكِيَاتٌ نَامِيَاتُ
ጥሩ የሆኑ ሰላዋቶች (ጸሎቶች)
ንጹህና እየጨመሩ የሚሄዱ
غَالِيَاتٌ دَائِمَاتُ
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ውድና ዘላለማዊ የሆኑ
ለተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ ይሁኑ
وَسَلَامُ اللهِ يَتْرَى
عَطَّرَ الْكَوْنَ وَ مَرَّا
የአላህም ሰላምታ በተከታታይ
አጽናፉን አውዶ አለፈ
شَرَحَ الصَّدْرَ وَسَرَّا
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ልብን አስፋፋ አስደሰተም
ለተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ
وَعَلَى الصَّحْبِ الْأَفَاضِلْ
كُلُّ مِفْضَالٍ وَعَامِلْ
በተከበሩት ባልደረቦቻቸውም ላይ
ሁሉም ምግባረ-ሰናይና ሰራተኛ በሆኑት
بِكِتَابِ اللهِ قَائِلْ
وَكَذَا آلِ مُحَمَّدْ
በአላህ መጽሐፍ ተናጋሪ በሆኑት
እንዲሁም በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ
عُمَّ بِالرِّضْوَانِ رَبِّي
خَيْرَ صِدِّيقٍ وَصَحْبِ
ጌታዬ ሆይ በውዴታህ አዳርስ
ምርጥ እውነተኛውንና ባልደረባውን
وَكَذَا الْفَارُوقُ حِبِّي
سَكَنَا قُرْبَ مُحَمَّدْ
እንዲሁም ተወዳጁን አል-ፋሩቅን
ሁለቱም ከሙሐመድ አጠገብ ያረፉትን
عُمَّ ذَا النُّورَيْنِ رَبِّي
وَأَبَا السِّبْطَيْنِ حِبِّي
ጌታዬ ሆይ፣ የሁለቱ ብርሃን ባለቤትን አዳርስ
እና የሁለቱ የልጅ ልጆች አባት ተወዳጁን
ثُمَّ لِلْعَمَّيْنِ رَبِّي
ثُمَّ صَحْبًا لِمُحَمَّدْ
ከዚያም ለሁለቱ አጎቶች ጌታዬ ሆይ
ከዚያም ለሙሐመድ ባልደረቦች
عُمَّ لِلسِّبْطَيْنِ رَبِّي
آلِ خَيْرِ الْخَلْقِ طِبِّي
ጌታዬ ሆይ ለሁለቱ የልጅ ልጆች አዳርስ
የፍጥረታት ምርጥ ቤተሰቦች፣ መድሃኒቶቼ
وَكَذَا الزَّهْرَاءُ تُنْبِي
عَنْ كَمَالٍ فِي مُحَمَّدْ
እንዲሁም አዝ-ዘህራእ ታሳውቃለች
በሙሐመድ ውስጥ ስላለው ፍጽምና
عُمَّ سُهَّارَ اللَّيَالِي
كُلَّ مَنْ لِلْوِرْدِ تَالِي
ሌሊቱን ቆመው የሚያድሩትን አዳርስ
ዊርድን የሚያነቡትን ሁሉ
هُمْ رِجَالُ الِاتِّصَالِ
بِالْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
እነርሱ የግንኙነት ሰዎች ናቸው
ከተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ ጋር
عُمَّ سُكَّانَ الْبَرَارِي
وَالصَّحَارَى وَالْقِفَارِ
በምድረበዳ ነዋሪዎችን አዳርስ
በበረሃዎችና ባዶ ቦታዎች ያሉትን
كُلَّ مَجْذُوبٍ وَقَارِي
لِلصَّلَاةِ عَلَى مُحَمَّدْ
እያንዳንዱን መንፈሳዊ መስጥት ያለበትንና አነባቢን
በሙሐመድ ላይ ሰላዋት የሚያወርደውን
عُمَّ رَبِّي النَّاسِكِينَا
وَالْعِبَادَ الصَّالِحِينَا
ጌታዬ ሆይ አምላኪዎችን አዳርስ
እናም ደጋግ ባሪያዎችን
وَالرِّجَالَ الْوَاقِفِينَا
عِنْدَ مَوْلَانَا مُحَمَّدْ
የቆሙትንም ሰዎች
በጌታችን ሙሐመድ ፊት
وَبِهِمْ يَا رَبِّ نَصْرَا
دَائِمًا دُنْيَا وَأُخْرَى
በእነርሱም ጌታዬ ሆይ ድልን ስጠን
ሁልጊዜ በዚህች ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ
أَعْظِمَنْ يَا رَبِّ أَجْرَا
بِالْحَبِيبْ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ጌታዬ ሆይ ምንዳን አብዛልን
በተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ ምክንያት
رَبِّ رُدَّ الْحَاسِدِينَا
عَنْ أَذَانَا خَائِبِينَا
ጌታዬ ሆይ ምቀኞችን መልስልን
እኛን ከመጉዳት አክስረህ
كُنْ لَنَا عَوْنًا مُعِينَا
بِالْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ለእኛ ረዳትና አጋዥ ሁነን
በተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ አማካይነት
رَبِّ لَا تَجْعَلْ عِدَانَا
تَتَمَكَّنْ مِنْ أَذَانَا
ጌታዬ ሆይ ጠላቶቻችንን አታድርጋቸው
እኛን በመጉዳት ላይ ችሎታ ያላቸው
اكْسُهُمْ ثَوْبًا هَوَانَا
وَأَجِبْنَا بِمُحَمَّدْ
የውርደት ልብስን አልብሳቸው
በሙሐመድም ምክንያት ጸሎታችንን ተቀበለን
عَجِّلِ الْخَوْفَ إِلَيْهِمْ
وَكَذَا الْبَأْسَ عَلَيْهِمْ
ፍርሃትን ወደ እነርሱ አፍጥን
እንዲሁም መከራን በእነርሱ ላይ
وَكَذَا الشَّرَّ لَدَيْهِمْ
وَانْصُرَنْ آلَ مُحَمَّدْ
እንዲሁም ክፋትን በነርሱ ላይ
የሙሐመድንም ቤተሰቦች እርዳ
نَاظِمُ الدُّرِّ الْمُحَرَّرْ
صَالِحٌ مِنْ آلِ جَعْفَرْ
የዚህ የተስተካከለ ዕንቁ ገጣሚ
ከጃዕፈር ቤተሰብ የሆነው ሷሊህ ነው
رَاجِي فَضْلًا مِنْكَ أَكْبَرْ
بِالْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ከአንተ ትልቅን ጸጋ ተስፋ አድራጊ ነው
በተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ አማካይነት
يَرْجُو فَضْلًا لَنْ يَزُولَا
وَرِضَاءً وَقَبُولَا
ማያልቅን ጸጋ ተስፋ ያደርጋል
ውዴታንና ተቀባይነትንም
وَاتِّصَالًا وَوُصُولَا
لِلْحَبِيبِ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
ግንኙነትንና መድረስንም
ከተወዳጁ ጌታዬ ሙሐመድ ጋር
يَرْجُو فَضْلًا مِنْكَ رَبِّي
زَوْرَةَ الْمُخْتَارِ حِبِّي
ጌታዬ ሆይ ከአንተ ጸጋን ይመኛል
የተመረጡት ተወዳጄን ጉብኝት
كُلَّ عَامٍ بَيْنَ صَحْبِ
زَائِرِينَ مَوْلَايْ مُحَمَّدْ
በየዓመቱ ከጓደኞች ጋር ሆኖ
ጌታዬ ሙሐመድን ከሚጎበኙ ጋር
وَبِخَيْرٍ فِي الْخِتَامِ
نَبْتَغِي نَيْلَ الْمَرَامِ
በመጨረሻውም በመልካም መደምደሚያ
ፍላጎታችንን ማግኘት እንሻለን
بِجِوَارٍ لِلْمَقَامِ
فِي بَقِيعٍ يَا مُحَمَّدْ
ከቦታው አጠገብ በመሆን
በበቂዕ ውስጥ፣ ኦ ሙሐመድ