بِفَاطِمَةْ قَدْ صَفَا حَالِي
በፋጢማ ሁኔታዬ ጠራ።
Am
بِفَاطِمَةْ قَدْ صَفَا حَالِي وَنِلْتُ الْمَرَامْ
بِضْعَة مُحَمَّدْ حَبِيبِ اللهْ خَيْرِ الْأَنَامْ
በፋጢማ ሁኔታዬ ጠራ የፈለኩትንም ሁሉ አገኘሁ
የሰው ልጆች ሁሉ በላጭ የአላህ ወዳጅ የሙሐመድ ቁራጭ
أَعْلَى لَهَا اللهْ قَدْراً فِي الْعُلَا وَالْمَقَامْ
نِعْمَ الْبَتُولْ الْرَّضِيَّةْ نُورْ كُلِّ الْظَّلَامْ
አላህ በልዕልና እና በደረጃ ክብሯን አላቀላት
የታታቢዋና ተወዳጇ ጨለማን ሁሉ የምታበራው ብርሃን ምንኛ ድንቅ ነች
أُمِّ الْحَسَنْ وَالْحُسَيْنْ أَهْلِ الْمَرْقَى الْعِظَامْ
لَهُمْ عَطَايَا مِنَ الْمَوْلَى كِبَارٌ جِسَامْ
የታላቅ እርከን ባለቤት የሀሰን እና የሁሰይን እናት
ከጌታ ታላላቅና ግዙፍ መለኮታዊ ስጦታዎች ተሰጥተዋቸዋል
هُمْ سَادَةَ أَهْلِ الْجِنَانِ الْعَالِيَةْ يَا غُلَامْ
مَنْ حَبَّهُمْ صِدِقْ بَا يِسْكُنْ بِدَارِ الْسَّلَامْ
እነሱ የልዑል ጀነት ሰዎች ጌቶች ናቸው አንተ ወጣት ሆይ
በውነት የወደዳቸው በሰላም መኖሪያ ይኖራል
وَمَنْ تَعَلَّقْ بِهِمْ يَظْفَرْ بِنَيْلِ الْمَرَامْ
أَكْرَمْتِ يَا بِضْعَةَ أَحْمَدْ فَانْعَمِي بِالْتَّمَامْ
በእነሱ የተጠጋም ፍላጎቱን ሁሉ ያገኛል
የአሕመድ ቁራጭ ሆይ! ለጋስ ነሽና ውለታውን ሙሉ አድርጊው
وَامْنَحِي عَبْدَكُمْ فِي الْقُرْبْ أَعْلَى وِسَامْ
نَقُومْ بِحَمِلْ الْرَّيَاتِ الْهُدَ أَحْسَنْ قِيَامْ
ለባሪያሽም በቅርበት ታላቁን ኒሻን ስጪው
የቅኑ መንገድን ሰንደቅ አላማ በጥሩ ሁኔታ የማንሳት ኒሻን
تَعُمْ دَعْوَتُهْ فِي الْأَكْوَانْ كُلِّ الْأَنَامْ
نِلْبَسْ خِلَعْ إِرْثْ مَا يَصِفْ سَنَاهَا كَلَامْ
የነቢዩ ጥሪ በዓለማትና በሰው ልጆች ሁሉ እንዲዳረስ
ብርሃኑ በቃል የማይገለጽ የነቢዩን ውርስ ካባ እንጎናጸፋለን
يَا نُورْ قَلْبِي وَيَا أُمِّي عَلَيْكِ الْسَّلَامْ
فِي كُلِّ حَالٍ وَشَأْنٍ كُلِّ لَحْظَةْ دَوَامْ
የልቤ ብርሃን እናቴ ሆይ! ሰላም በአንቺ ላይ ይሁን
በሁኔታዎች ሁሉ፣ በጉዳዮች እና በሁሉም ቅጽበት ዘላቂ የሆነ ሰላም
عَلَيْكِ صَلَّى إِلَهِي مَعَ أَبِيكِ الْإِمَامْ
إِمَامْ كُلِّ الْوَرَى فِي كُلِّ خَاصٍّ وَعَامْ
አምላኬ በአንቺና በኢማሙ አባትሽ ላይ ሰላት ያውርድ
በልዩውም ሆነ በጠቅላላው የፍጡራን ሁሉ መሪ በሆኑት
الْشَّافِعِ الْمُبْتَغَ يَوْمَ الْلِّقَاءْ وَالْزَّهَامْ
يَوْمِ الْمَلَائِكْ تُنَادِي جَمِعْ كُلِّ الْأَنَامْ
በመገናኛውና በግርግሩ ቀን የሚፈለጉት አማላጅ
መላእክት በጉባኤው ለሰው ልጆች ሁሉ በሚጣሩበት ቀን
غُضُّوا أَبْصَارَكُمْ تَمُرْ بِنْتِ الْنَّبِيِ بِالْسَّلَامْ
وَنَكِّسُوا رُؤُوسَكُمْ مَا أَعْظَمَهْ وَاللهْ مَقَامْ
"አይኖቻችሁን ዝቅ አድርጉ የነቢዩ ልጅ በሰላም ትለፍ"
"ራሳችሁንም ዝቅ አድርጉ" በአላህ ይሁንብኝ ምንኛ ታላቅ ደረጃ ነው!
تِذَكَرِينِي مَعَكِ أَعْبُرْ وَمَنْ لَهُ ذِمَامْ
حَاشَاكِ يَا أُمَّنَا تِنْسِينْ هَذَا الْغُلَامْ
በአንቺ ጥበቃ ስር ከአንቺ ጋር እንዳልፍ አስቢኝ
እናታችን ሆይ! ይህንን ልጅሽን መርሳት ከአንቺ ፈጽሞ አይጠበቅም
مَحْسُوبَكُمْ يَرْتَجِيهْ مِنْكُمْ بِهِ الْإِهْتِمَامْ
أَنْتُمْ مَرَامُهْ وَمَقْصُودُهْ وَنِعْمَ الْمَرَامْ
ልጅሽ የእናንተን ትኩረት ተስፋ ያደርጋል
እናንተ ግቡና ፍላጎቱ ናችሁ፣ ምንኛ ድንቅ ፍላጎት ነው!
يَا بِنْتَ طه فُؤَادِي فِي مَحَبَّتِكْ هَامْ
وَاللهْ أَنْتُمْ مُرَادِي فِي الْدُّنَا وَالْقِيَامْ
የጣሀ ልጅ ሆይ! ልቤ በፍቅርሽ ተነድፏል
በአላህ ይሁንብኝ እናንተ በዚህችም ሆነ በትንሳኤው ቀን ፍላጎቴ ናችሁ
وَمَا أَنَا إِلَّا بِكُمْ يَا سَادَتِي يَا كِرَامْ
عَلَيْكِ مَعَ وَالِدِكْ أَزْكَى الْصَّلَاةْ وَالسَّلَامْ
የተከበራችሁ ጌቶቼ ሆይ! እኔ ያለ እናንተ ምንም አይደለሁም
በአንቺና በወላጆችሽ ላይ ንጹህ ሰላትና ሰላም ይውረድ
وَأَهْلِ الْكِسَاءْ وَأَهْلِ بَيْتِهْ عَالِيِّينَ الْمَقَامْ
وَالْصَّحْبْ أَجْمَعْ وَمَنْ عَلَى هُدَاهْ اِسْتَقَامْ
በካባው ሰዎችና በቤተሰቦቻቸው ላይ፤ የከፍተኛ ደረጃ ባለቤቶች
በባልደረቦቻቸው ሁሉና በቅኑ መንገድ በጸኑት ላይም