مَنْ مِثْلُ أحمد
እንደ አህመድ ማን ነው?
Am
Am
اللهْ اللهُ اللهْ اللهُ
اللهْ اللهُ تَبَارَكَ اللهُ
አላህ አላህ አላህ አላህ
አላህ አላህ አላህ ተባረከ
مَنْ مِثْلُ أَحْمَدَ فِي الكَوْنَيْنِ نَهْوَاهُ
بَدْرٌ جَمِيعُ الوَرَى فِي حُسْنِهِ تَاهُوا
በሁለቱ ዓለም እንደ አህመድ ያለ ማን አለ የምንወደው?
በውበቱ ፍጥረት ሁሉ የፈዘዘለት ሙሉ ጨረቃ ነው
مَن مِثْلُهُ وَ إِلَهُ الْعَرْشِ شَرَّفَهُ
بِالْخَلْقِ وَ الْخُلْقِ إِنَّ اللَّهَ أَعْطَاهُ
የዐርሹ ጌታ ያከበረው እንደርሱ ማን አለ?
በስነ-ፍጥረትና በስነ-ምግባር አላህ ሰጥቶታል
وَالشَّمْسُ تَخْجَلُ مِنْ أَنْوَارِ طَلْعَتِهِ
حَارَتْ عُقُولُ الْوَرَى فِي فَهْمِ مَعْنَاهُ
ፀሐይም ከፊቱ ብርሃን የተነሳ ታፍራለች
የፍጥረት አእምሮ የእርሱን ምንነት ለመረዳት ተጨነቀ
تَبَارَكَ اللَّهُ مَا أَحْلَى شَمَائِلَهُ
حَازَ الْجَمَالَ فَمَا أَبْهَى مُحَيَّاهُ
አላህ ተባረከ፤ ስብእናው ምንኛ ጣፈጠ
ውበትን ሁሉ ሰበሰበ፤ ፊቱ ምንኛ አበራ
يَا عُرْبَ وَادِي النَّقَى يَا أَهْلَ كَاظِمَةٍ
فِي حَيِّكُمْ قَمَرٌ فِي الْقَلْبِ مَثْوَاهُ
የዋዲ አል-ኑቃ ዓረቦች ሆይ የካዚማ ሰዎች ሆይ
በመንደራችሁ ውስጥ በልብ የሚኖር ጨረቃ አለ
صَلَّى عَلَيْهِ إِلَهُ الْعَرْشِ مَا طَلَعَتْ
شَمْسٌ وَ مَا حَدْحَدَ الْحَادِي مَطَايَاهُ
የዐርሹ ጌታ ሰላት ያውርድበት ፀሐይ በወጣች ቁጥር
ግመል ነጂውም ግመሎቹን በመራቸው ቁጥር
اللهُ بِالْمَدْحِ لِلْمُخْتارِ مَنَّ عَلَيّْ
عَسَى يُرى لِيَ بَيْنَ المَادِحِيْنَ حَلَي
አላህ ምርጡን በማወደስ በእኔ ላይ ዋለልኝ ውለታ
ምናልባት በአውዳሾቹ መካከል ክብሬ ይታይ ዘንድ
إِذَا أَتَيْتُ لِأَقْرَا الصُّحْفَ مِنْ عَمَلِيْ
مَالِي سِوَى مَنْ لَهُ فَضْلٌ يُشِيْرُ إِلَىّ
የስራ መዝገቤን ላነብ በመጣሁ ጊዜ
ጸጋው ወደ እኔ ከሚጠቁመኝ ጌታ ውጪ ሌላ የለኝም
مُحَمَّدٌ سَيِّدُ الكَوْنَيْنِ وَالثَّقَلَيْـنِ
وَالفَرِيقَيْنِ مِنْ عُرْبٍ وَمِنْ عَجَمِ
ሙሐመድ የሁለቱ ዓለማትና የሰውና ጋኔን ጌታ ነው
የሁለቱም ወገኖች የዓረብም ይሁን የዐጀም
هُوَ الحَبِيبُ الذِّي تُرْجَى شَفَاعَتُهُ
لِكُلِّ هَوْلٍ مِنَ الأَهْوَالِ مُقْتَحَمِ
እርሱ አማላጅነቱ የሚከጀል ውድ ወዳጅ ነው
በድንገት ለሚመጡ አስፈሪ ክስተቶች ሁሉ
نَبِيُّنَا الآمِرُ النَّاهِي فَلاَ أَحَدٌ
أَبَرَّ فِي قَوْلِ لاَ مِنْهُ وَلاَ نَعَمِ
ነቢያችን አዛዥና ከልካይ ነው፤ ማንም የለም
"አይ" ወይም "አዎ" በማለት ከእርሱ የበለጠ እውነተኛ
كَالزَّهْرِ فِي تَرَفٍ وَالبَدْرِ فِي شَرَفٍ
وَالبَحْرِ فِي كَرَمٍ وَالدَّهْرِ فِي هِمَمِ
በውበት እንደ አበባ በልዕልና እንደ ሙሉ ጨረቃ
በቸርነት እንደ ባህር በቁርጠኝነት እንደ ዘመን
يِا رَبِّ بِالمُصْطَفَى بَلِّغْ مَقَاصِدَنَا
وَاغْفِرْ لَنَا مَا مَضَى يَا وَاسِعَ الكَرَمِ
ጌታዬ ሆይ በሙስጠፋ ፍላጎታችንን አድርስልን
ያለፈውንም ማረን አንተ ቸርነትህ ሰፊ የሆንክ
وَاغْفِرْ إِلَهِي لِكُلِ المُسْلِمِينَ بِمَا
يَتْلُونَ فِي المَسْجِدِ الأَقْصَى وَفِي الحَرَمِ
አምላኬ ሆይ ለሙስሊሞች ሁሉ ማረን
በአቅሷ መስጂድና በሐረም በሚቀሩት ቅዱስ ቃላት
بِجَاهِ مَنْ بَيْتُهُ فِي طَيْبَةٍ حَرَمٌ
وَإسْمُهُ قَسَمٌ مِنْ أَعْظَمِ الْقَسَمِ
በጣይባ ቤቱ ክቡር በሆነው ነቢይ ማዕረግ
ስሙም ከታላላቅ መሐላዎች አንዱ በሆነው