رَسُولَ إِلَهِ الْعَالَمِينَ تَعَالَى
የልዑል የዓለማት ጌታ መልእክተኛ
Am
Am
رَسُولَ إِلَــهِ الْعَالَمِيـــــنَ تَعَالَـى
خَدِيمُكَ نَادَى يَا رَسُولُ تَعَـــالاَ
የዓለማት ጌታ መልዕክተኛ ሆይ! ልዑል የሆንክ
አገልጋይህ ተጣራ፡- አንቱ መልዕክተኛ ሆይ! ቀረብ በሉልኝ!
خَدِيمُكَ نَادَى يَا رَسُولُ فَلاَ أُرَى
فَقِيرًا إِلَى غَيْــرِ الْإِلَـــهِ تَعَالَــى
አገልጋይህ ተጣራ፡- አንቱ መልዕክተኛ ሆይ! እንግዲህ አልታይ
ከልዑል አምላክ በቀር ለማንም ችግረኛ ሆኜ
خَدِيمٌ بِأَقْصَى الْغَرْبِ يَدْعُو مُحَمَّــدًا
وَلَيْسَ يَرَى غَيْرَ الْرَّسُـــولِ ثِمَـالاَ
በሩቅ ምዕራብ ያለ አገልጋይ ሙሐመድን ይጠራል
ከመልዕክተኛው በቀር ሌላ መጠጊያ የማያይ ሲሆን
خَدِيمٌ ثَـوَى بِالْبَابِ وَهْــــوَ مُؤَمِّــلٌ
إِيَابًا كَرِيمًــــا وَهْـوَ جَيْــرِ أَطَــالاَ
ደጃፍዎ ላይ የቆየ አገልጋይ ነው፤ እርሱም ተስፋ ያደርጋል
የተከበረ አቀባበልን፣ ምንም እንኳን ቆይታው ቢረዝምም
تَصَاغَرَ عِنْدِي غَيْرُ أَحْمَــدَ إِنَّنِــي
أُرَجِّي مِنَ الْهَــادِي الْعِبَــادِ مَنَـالاَ
ከአሕመድ በቀር ሌላው ሁሉ በዓይኔ አነሰ፤ እኔ በእርግጥም
የባሮች መሪ ከሆኑት ዘንድ ስጦታን ተስፋ አደርጋለሁና
كَرِيمَ الْسَّجَايَا وَاسِعَ الْجُودِ مَا تَرَى
لِضَيْـــــفِ كَرِيــمٍ قَــدْ أَجَادَ مَقَــالاَ
የመልክ ባሕርይ ባለቤትና ሰፊ ለጋስ ሆይ! ምን ይመስልዎታል
ልመናውን አሳምሮ ላቀረበው ለዚያ ለጋስ እንግዳ
فَهَبْهُ عَلَى مِقْدَارِ كَفِّــكَ مُصْطَفَى الْ
بَرَايَــا عَطَاءً لاَ يَخَــافُ زَوَالاَ
እንደ ለጋስ እጅዎ መጠን ስጡት የፍጡራን ምርጥ ሆይ
መቋረጥን የማይሰጋ ታላቅ ስጦታን
فَفِي كُلِّ حَيٍّ قَدْ خَبَطْتَ بِنِعْمَــةٍ
وَإِنِّي كَشأْسٍ قَــدْ أَرُومُ نَــوَالاَ
በሁሉም ሕያው ላይ ጸጋን አዝንበዋልና
እኔም እንደ ምስኪን ፈላጊ ልግስናዎን እከጅላለሁ
عَلَيْكَ صَـــلاَةُ اللّٰهِ ثُــمَّ سَلاَمُــهُ
وَتَشْمَلُ أَصْحَابَ الْنَّبِـــيِّ وَآلاَ
የአላህ ሰላትና ሰላም በእርስዎ ላይ ይሁን
የነቢዩን ባልደረቦችና ቤተሰቦችንም የሚጨምር