قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
አብሪው ሙሉ ጨረቃ ወጣ
Am
Am
قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
بِمَوْلِدِ الْهَـادِي الْبَشِيـرْ
አበራ ያበራው ሙሉ ጨረቃ
በመሪውና በአብሳሪው ልደት
أَهْلاً وَسَهْلاً بِالْإِمَامْ
الْمُصْطَفَى بَـدْرِ الْتَّمَـامْ
እንኳን ደህና መጣህ ለኢማሙ
ለተመረጡት ፍጹም ሙሉ ጨረቃ
شَفِيعِنَا يَوْمَ الْزِّحَـامْ
أَرْسَلَـهُ الْـرَّبُّ الْقَدِيـرْ
በጭንቁ ቀን አማላጃችን
ሁሉን ቻይ በሆነው ጌታ የተላኩ
قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
بِمَوْلِدِ الْهَـادِي الْبَشِيـرْ
አበራ ያበራው ሙሉ ጨረቃ
በመሪውና በአብሳሪው ልደት
بُشْرَى لَنَا نِلْنَا الْمَرَامْ
بِطَـهَ مُعْتَلِـى الْمَقَـامْ
ብስራት ለእኛ ፍላጎታችንን አገኘን
ከፍተኛ ማዕረግ ባላቸው በጣሀ
شَرَّفَـهُ رَبُّ الْأَنَـامْ
فَلَـمْ يَكُـنْ لَـهُ نَظِيـرْ
የሰው ልጆች ጌታ አከበራቸው
ለእሳቸው አምሳያ የለምና
قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
بِمَوْلِدِ الْهَـادِي الْبَشِيـرْ
አበራ ያበራው ሙሉ ጨረቃ
በመሪውና በአብሳሪው ልደት
يَا ذَا الْجَلَالِ يَا مُجِيبْ
عَبْدٌ دَعَـاك لَا يَخِيـبْ
የልቅና ባለቤት ሆይ ጸሎት ተቀባይ
የጠራህ ባሪያ ፈጽሞ አይከስርም
بِحُرْمَةِ الْنَّبِيِّ الْحَبِيبْ
يَسِّرْ لَنَا الْأَمْـرَ الْعَسِيـرْ
በተወዳጁ ነቢይ ክብር
አስቸጋሪውን ነገር ሁሉ አግራልን
قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
بِمَوْلِدِ الْهَـادِي الْبَشِيـرْ
አበራ ያበራው ሙሉ ጨረቃ
በመሪውና በአብሳሪው ልደት
أَدْعُوكَ يَا رَبَّ الْأَنَامْ
أَمِتْنَا عَلَى حُسْنِ الْخِتَـامْ
የሰው ልጆች ጌታ ሆይ እጠራሃለሁ
በመልካም መደምደሚያ ግደለን
وَأَسْكِنَـا فِي دَارَ الْسَّلَامْ
لِبَاسُنَـا فِيهَـا حَرِيرْ
በሰላም ቤት አኑረን
ልብሳችንም በዚያ የሐር ነው
قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
بِمَوْلِدِ الْهَـادِي الْبَشِيـرْ
አበራ ያበራው ሙሉ ጨረቃ
በመሪውና በአብሳሪው ልደት
أَجِبْ دُعَانَا يَا أَحَدْ
وَاسْمَعْ نِدَانَا يَا صَمَدْ
ጸሎቴን ተቀበል አንተ አንድ የሆንክ
ጥሪዬንም ስማ የሁሉ መጠጊያ
يَا دَائِماً عَلَى الْأَبَـدْ
أَنْـتَ الْمُهَيْمِـنُ الْخَبِيـرْ
ለዘላለም ዘላቂ የሆንክ ሆይ
አንተ ተቆጣጣሪና ሁሉን አዋቂ ነህ
قَدْ أَشْرَقَ الْبَدْرُ الْمُنِيرْ
بِمَوْلِدِ الْهَـادِي الْبَشِيـرْ
አበራ ያበራው ሙሉ ጨረቃ
በመሪውና በአብሳሪው ልደት
أَهْدِي الْتَّحِيَّةْ وَالْسَّلَامْ
لِلْمُجْتَبَـى خَيْرِ الْأَنَـامْ
ሰላምታና ውዳሴን አበረክታለሁ
ለተመረጡትና ከሰው ሁሉ በላጭ ለሆኑት
والْآلِ وَالْصَّحْبِ الْكِرَامْ
مَا أَمْطَرَ الْمَطْرُ الْغَزِيرْ
ለተከበሩ ቤተሰቦቻቸውና ባልደረቦቻቸው
ዶፍ ዝናብ እስከሚዘንብ ድረስ