فَيَا نَفَحَاتِ اللهِ يَا عَطَفَاتِهِ
O Divine Breaths of Allah, O His Affections
Am
فَيَا نَفَحَاتِ اللهِ يَا عَطَفَاتِهِ
وَيَا جَذَبَاتِ الْحَقِّ جُودِي بِزَوْرَةِ
የጌታ መዓዛዎችና ርህራሄዎቹ ሆይ!
የእውነትም ስበት ሆይ! በጉብኝት ቸሩልን።
وَيَا نَظَرَاتِ اللّهِ يَا لَحَظَاتِهِ
وَيَا نَسَمَاتِ اللُّطْفِ أُمِّى بِهَبَّةِ
የአላህ እይታዎችና ትኩረቶቹ ሆይ!
የቸርነት ነፋሻማዎች ሆይ! በስጦታ ንፈሱ።
وَيَا غَارَةَ الرَّحْمَانِ جُدِّىْ بِسُرْعَةِ
إِلَيْنَا وَحُلِّى عَقْدَ كُلِّ مُلِمَّةِ
የረህማን እርዳታ ሆይ! በፍጥነት ድረሽልን
ወደ እኛም ኑና የጭንቅን ሁሉ ቋጠሮ ፍቺ።
وَيَا رَحْمَةَ الرَّبِّ الرَّحِيْمِ تَوَجَّهِىْ
وَأَحْيِىْ بِرُوْحِ الفَضْلِ كُلَّ رَمِيْمَةِ
የሩህሩሁ ጌታ እዝነት ሆይ! ፊቱን ወደ እኛ አዙር
በጸጋውም መንፈስ የበሰበሰውን ሁሉ ሕያው አድርግ።
وَيَاكُلَّ أَبْوَابِ الْقَبُولِ تَفَتَّحِىْ
فَإِنَّ مَطَايَا الْقَصْدِ نَحْوَكَ أَمَّتِ
የተቀባይነት በሮች ሁሉ ሆይ! ተከፈቱ
የፍላጎት ግመሎች ወደ እናንተ አምርተዋልና።
وَيَاسُحُبَ الْجُوْدِ الْإِلَهِيِّ أَمْطِرِىْ
فَإِنَّ أَكُفَّ الْمَحْلِ تِلْقَاكِ مُدَّتِ
የመለኮታዊ ልግስና ደመናዎች ሆይ! አዝንቡ
የድርቅ መዳፎች ወደ እናንተ ተዘርግተዋልና።
بِحُرْمَةِ هَادِيْنَا وَمُحْيِيْ قُلُوْبِنَا
وَمُرْشِدِنَا نَهْجَ الطَّرِيْقِ الْقَوِيْمَةِ
የመሪያችንና የልባችን ሕያው አድራጊ በሆነው ክብር
ወደ ቀጥተኛው መንገድ መሪያችን በሆነው።
دَعَانَا إِلَى حَقٍّ بِحَقٍّ مُنَزَّلٍ
عَلَيْهِ مِنَ الرَّحْمَانِ أَفْضَلَ دَعْوَةِ
በተወረደ እውነት ወደ እውነት ጠራን
ከአል-ራህማን ዘንድ በሆነችው በላጭ ጥሪ።
أَجَبْنَا قَبِلْنَا مُذْعِنِيْنَ لِأَمْرِهِ
سَمِعْنَا أَطَعْنَا عَنْ هُدىً وَبَصِيْرَةِ
ለትእዛዙ ታዛዥ ሆነን መለስን፤ ተቀበልንም
በቅን መንገድና በግልጽ እይታ ሰማን ታዘዝንም።
فَيَارَبِّ ثَبِّتْنَا عَلَى الْحَقِّ وَالْهُدَى
وَيَارَبِّ اِقْبِضْنَا عَلَى خَيْرِ مِلَّةِ
ጌታ ሆይ! በእውነትና በቅን መንገድ ላይ አጽናን
ጌታ ሆይ! በበላጭ ሃይማኖት ላይ ነፍሳችንን ውሰድ።
وَعُمَّ أُصُوْلاً وَالْفُرُوْعَ بِرَحْمَةٍ
وَأَهْلاً وَأَصْحَاباً وَكُلَّ قَرَابَةِ
ስሮችንና ቅርንጫፎችን በእዝነትህ አዳርስ
ቤተሰብን፣ ባልደረቦችንና ዘመዶችንም ሁሉ።
وَسَائِرِ أَهْلِ الدِّيْنِ مِنْ كُلِّ مُسْلِمٍ
أَقَامَ لَكَ التَّوْحِيْدَ مِنْ غَيْرِ رِيْبَةِ
ሌሎችንም ሃይማኖተኞች ከሙስሊሞች ሁሉ
ያለ ምንም ጥርጥር ተውሂድን ላንተ ያቆሙትን።
وَصَلِّ وَسَلِّمْ دَائِمَ الدَّهْرِ سَرْمَداً
عَلَى خَيْرِ مَبْعُوْثٍ إِلَى خَيْرِ أُمَّةِ
ዘላለም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሰላትና ሰላምን አውርድ
ወደ በላጭ ኡመት በተላኩት በላጭ መልክተኛ ላይ።
مُحَمَّدٍ الْمَخْصُوْصِ مِنْكَ بِفَضْلِكَ
الْعَظِيْمِ وَإِنْزَالِ الْكِتَابِ وَحِكْمَةِ
በታላቅ ችሮታህ ከአንተ ዘንድ ለተለዩት ሙሐመድ
መጽሐፍንና ጥበብን በማውረድ ለተከበሩት።