يَمِّمْ نَحْوَ الْمَدِينَةْ تَرَى الْأَنْوَارْ
ወደ መዲና አምራ ብርሃናትን ታያለህ
Am
Am
يَمِّمْ نَحْوَ الْمَدِينَةْ تَرَى الْأَنْوَارْ
وَاقْصُدْ حِمَى نَبِيِّنَا طَهَ الْمُخْتَارْ
ወደ መዲና አቅና ብርሃናትን ታያለህና
የተመረጠው የነቢያችን የጣሀን ጥገኝነት ፈልግ
مُحَمَّدْ يَا أَبَا الْزَّهْرَا نَرْجُو نَظْرَةْ
أَرَى الْقُبَّةَ الْخَضْرَا لَيْلًا وَنَهَارْ
ሙሐመድ ሆይ የዘህራ አባት እይታህን ተስፋ እናደርጋለን
ያችን አረንጓዴ ጉልላት በቀንም በሌሊት እመለከታለሁ
مُحَمَّدْ يَا أَبَا الْقَاسِمْ إِنِّي هَائِمْ
عَسَى تَقْبَلْنِيْ خَادِمْ أَنَا وَالْحُضَّارْ
ሙሐመድ ሆይ የቃሲም አባት እኔ በፍቅርህ ተነድፌአለሁ
እኔንም ሆነ እዚህ የተገኙትን አገልጋይ አድርገህ ትቀበለን ዘንድ
فَامْدُدْ يَدَكْ وَالْبَاعَا وَالْذِّرَاعَا
وَاطْلُبْ مِنْهُ الْشَّفَاعَةْ وَقْتَ الْأَسْحَارْ
እጅህን፣ ክንድህንና ትከሻህን ዘርጋ
በሌሊትም መጨረሻ ከእርሱ ምልጃን ለምን
وَقِفْ حَوْلَ الْضَّرِيحِ يَا فَصِيحِ
وَاغْسِلْ قَلْبَ الْجَرِيحِ مِنَ الْأَْكْدَارْ
አንተ አንደበተ ርቱዕ ሆይ በክቡር መቃብራቸው ዙሪያ ቁም
የቆሰለውንም ልብ ከጭንቀትና ከሀዘን እጠበው