مَا لِي سِوَاكْ هَمْ وَأَنْتَ تَعْلَمْ
ከአንተ በቀር ሌላ ሐሳብ የለኝም፤ አንተም ታውቃለህ።
Am
Am
مَا لِي سِوَاكْ هَمْ وَأَنْتَ تَعْلَمْ
فَالْقُرْبُ مَغْنَمْ وَالْبُعْدُ مَغْرَمْ
አንተን እንጂ ሌላ ሃሳብ የለኝም አንተም ታውቃለህ
መቃረብህ ትርፍ ነው መራቅህ ግን ኪሳራ
خُذْنِي إِلَيْكَ بَيْنَ يَدَيْكَ
حُسِبْتُ عَلَيْكَ فِي كُلِّ مَا أَعْلَمْ
ወደ አንተ ውሰደኝ በእቅፍህ ውስጥ አድርገኝ
በሚታወቀው ሁሉ ያንተ እንደሆንኩ ተቆጥሬያለሁና
أَنْتَ مُرَادِي فَكُنْ لِيْ هَادِي
فَالْقَلْبُ صَادِي فَزِلْ لِيْ ذَا الْهَمْ
አንተ ፍላጎቴ ነህና መሪ ሁነኝ
ልቤ ተጠምቷልና ይህን ሃዘን አስወግድልኝ
مَنْ ذَا يَكُنْ لِي إِنْ لَمْ تَكُنْ لِي
تَرَى لِذُلِّي وَأَنْتَ أَرْحَمْ
አንተ ለእኔ ካልሆንክልኝ ማን ይሆንልኛል
ዝቅ ማለቴን ታያለህ አንተም እጅግ አዛኝ ነህ
كَمْ ذَا أُنَادِي يَا خَيْرَ هَادِي
يَكْفِي بُعَادِي فَالْجُودُ قَدْ عَمْ
አንተ ምርጥ መሪ ሆይ! ስንት ጊዜ ጠራሁህ
መራራቁ ይብቃኝ ቸርነትህ ሁሉን አዳርሷልና
نُورُ الْوِصَالِ مَهْرُهُ غَالِي
سِوَاكَ مَا لِي جُدْ وَتَكَرَّمْ
የውህደት ብርሃን ጥሪቱ ውድ ነው
ከአንተ በቀር ማንም የለኝም ቸርነትህን ለግሰኝ
قُرْبِي وَبُعْدِي سِيَّانِ عِنْدِي
لِأَنَّ رُشْدِي فِيمَا تَقَسِّمْ
መቅረብና መራቅ ለእኔ እኩል ናቸው
ምክንያቱም ቅንነቴ አንተ በከፈልከው ውስጥ ነውና
فَاجْعَلْ هِبَاتِي رُوحَ الْحَيَاةِ
حَبِيبْ ذَاتِي طه الْمُعَلِّمْ
ስጦታዎቼን የህይወት መንፈስ አድርጋቸው
የነፍሴ ወዳጅ አስተማሪው ጣሀ ናቸው
تَعْلَمْ لِقَصْدِي حِبِّي وَوُدِّي
فَكُنْ لِلْكُرْدِي فِي كُلِّ مَغْنَمْ
አላማዬን፣ ፍቅሬንና ውዴታዬን ታውቃለህ
በሁሉም ስኬት ላይ ለኩርዲይ ሁንለት
صَلَاةُ رَبِّي لِحَبِيبِ قَلْبِي
طه الْمُرَبِّي عَلَيْهِ سَلَّمْ
የጌታዬ እዝነት በልቤ ወዳጅ ላይ ይውረድ
መሪው ጣሀ ላይ ሰላም ይስፈን