خُذْ مَا صَفَا وَدَعِ الْكَدَر
የጠራውን ውሰድ፤ የደፈረሰውን ተው።
Am
Am
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
خُذْ مَا صَفَا وَدَعِ الْكَدَرْ
وَكِلِ الْأُمُورَ إلى الْقَدَرْ
ጥሩውን ያዝ ዝቃጩን ተው
ነገሮችንም ሁሉ ለአላህ ውሳኔ (ቀደር) አሳልፈህ ስጥ
مَهْمَا غُلِبْتَ كَمَا أَمَرْ
هَادِي الْوَرَى خَيْرُ الْبَشَرْ
ምንም እንኳ ብትሸነፍ እርሳቸው እንዳዘዙት አድርግ
የፍጥረታት መሪ የሰው ልጆች ሁሉ በላጭ
إِنَّ الْأُمُورَ جَرَى بِهَا
قَلَمٌ عَلَى الْلَّوْحِ الْأَغَرْ
ነገሮች ሁሉ በእርግጥ ተከናውነዋል
በብርሃናማው ሰሌዳ (ለውህ) ላይ ባለ ብዕር
فِي سَابِقِ الْعِلْمِ الْقَدِيمْ
مِنْ قَبْلِ إِيجَادِ الْصُّوَرْ
ምስሎች ከመፈጠራቸው በፊት
በቀደመውና ጥንታዊው እውቀት
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
وَدَعِ الْهُمُومَ فَإِنَّهَا
يَا صَاحِبِي مَحْضُ الْضَّرَرْ
ጭንቀትንም ተዋት እርሷማ
ወዳጄ ሆይ ንጹህ ጉዳት ብቻ ናትና
وَاغْنَمْ زَمَانَكَ وَاسْتَرِحْ
مِنْ لَوْ وَلِمْ تَلْقَ الْظَّفَرْ
ጊዜህን ተጠቀምና እረፍት አግኝ
ከ"ቢሆንስ" እና "ለምን" ርቀህ ድልን ትቀዳጃለህ
وَارْجِعْ إِلَى اللَّهِ إِذَا
مَالَحَّ خَطْبٌ أَوْ عَصَرْ
ወደ አላህም ተመለስ በየጊዜው
መከራ ቢጫንህ ወይም ቢያጨንቅህ
وَإِذَا بُلِيتَ بِمِحْنَةٍ
فَاصْبِرْ لَهَا فِيمَنْ صَبَرْ
በፈተናም በተሞከርክ ጊዜ
በትዕግስተኛኞች ዘንድ ሆነህ ታገስ
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
مِنْ كُلِّ بَرٍّ مُوقِنٍ
مُتَوَقِّرٍ عِنْدَ الْغِيَرْ
እርግጠኛ ከሆኑ ደግ ነፍሳት ሁሉ ሁን
የጊዜ መለዋወጥ ሲመጣ ከሚረጋጉት
وَإِذَا خُصِصْتَ بِنِعْمَةٍ
فَاشْكُرْ مَعَ مَنْ قَدْ شَكَرْ
በጸጋ (ኒዕማ) በተለየህ ጊዜ
ከአመስጋኞች ጋር ሆነህ አመስግን
لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينْ
تُعْطَ الْمَزِيدَ كَمَا ذَكَرْ
ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ምስጋና አቅርብ
እርሱ እንደጠቀሰው ጭማሪ ይሰጥሃልና
وَاعْمَلْ لِنَفْسِكَ صَالِحًا
تَنْجُو بِهِ مِنْ كُلِّ شَرْ
ለራስህም መልካም ስራን ስራ
ከክፉ ነገር ሁሉ በእርሱ ትድን ዘንድ
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
وَتَفُوزُ بِالْحُسْنَى وَبِالْــــ
ــــجَنَّاتِ دَارِ الْمُسْتَقَرْ
በመልካሚቱ ትድናለህ እንዲሁም
የመኖሪያ ቤት በሆኑት ገነቶች (ጀናህ)
دَارِ الْبَقَا دَارِ الْنَّعِيمْ
دَارِ الْكَرَامَةِ وَالْنَّظَرْ
የዘላለም ቤት የጸጋ ቤት
የክብር ቤትና ጌታን የማየት ቤት
وَأَعِدَّ زَادَكَ لِلْمَعَادْ
مِنْ قَبْلِ يَفْجَاكَ الْحَذَرْ
ለመመለሻ ቀን ስንቅህን አዘጋጅ
ሞት በድንገት ሳይመጣብህ በፊት
فَالْمَوْتُ آتٍ عَنْ قَرِيبْ
وَلَعَلَّ يَوْمَكَ قَدْ حَضَرْ
ሞት በቅርቡ ይመጣልና
ምናልባትም ቀጠሮህ ዛሬ ደርሶ ይሆናል
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
يَا رَبُّ أَنْتَ الْمُبْتَغَى
وَالْمُرْتَجَى وَالْمُدَّخَرْ
ጌታ ሆይ! አንተ ተፈላጊው ነህ
ተስፋ የሚጣልብህና ለቀን የተከማቸህ
يَا رَبَّنَا فَاسْتُرْ وَسَا
مِحْ أَنْتَ أَكْرَمُ مَنْ سَتَرْ
ጌታችን ሆይ! ነውራችንን ደብቅልን ይቅርም በለን
አንተ ከሸፋኞች ሁሉ በላጭ ቸር ነህና
يَا رَبَّنَا وَانْظُرْ إِلَيـْــــ
ـــنَا أَنْتَ أَحْسَنُ مَنْ نَظَرْ
ጌታችን ሆይ! በእዝነት ተመልከተን
አንተ ከተመልካቾች ሁሉ በላጭ ነህና
يَا رَبَّنَا وَاخْتِمْ لَنَا
بِالْخَيْرِ إِنْ حَانَ الْسَّفَرْ
ጌታችን ሆይ! መጨረሻችንን በመልካም አድርግልን
የጉዞው (የሞት) ጊዜ ሲቃረብ
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
ثُمَّ الصَّلَاةُ عَلَى الرَّسُولْ
خَيْرِ الْبَرِيَّةِ مِنْ مُضَرْ
ከዚያም ሶላት (ሰላምታ) በመልእክተኛው ላይ ይሁን
ከሙደር ነገድ በሆኑት የፍጥረት ሁሉ በላጭ
خَتْمِ الْنَّبِيِّينَ الْكِرَامْ
نِعْمَ الْمَصَابِيحُ الْغُرَرْ
የከበሩ ነቢያት መደምደሚያ
ያማሩና ብርሃናማ የሆኑ ፋናዎች
وَآلِهِ وَاصْحَابِهِ
وَالتَّابِعِينَ عَلَى الْأَثَرْ
በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ
እንዲሁም ፈለጋቸውን በተከተሉት ላይ
مَا هَبَّتِ الـــنَّسَمَاتُ بِالْــــ
ــــعَرْفِ الْمُعَنْبَرِ في الْسَّحَرْ
ነፋሻማ ነፋሶች እስ ነፈሱ ድረስ
በሌሊት መጨረሻ የዐንበር ሽታን ይዘው
يَا رَبَّنَا يَا رَبَّنَا
غِثْنَا بِقُرْبِ الـْمُصْطَفَى
ጌታችን ሆይ ጌታችን ሆይ
በተመረጡት ሙስጠፋ ቅርበት እርዳታን ለግሰን
وَ ارْحَمْ إِلَهِي ضَعْفَنَا
بِٱلْمُصْطَفَىٰ خَيْرِ ٱلْبَشَرْ
አምላኬ ሆይ ደካማነታችንን እዘንልን
በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት በሙስጠፋ
أَوْ غَرَّدَتْ وُرْقُ الْحِمَى
فَوْقَ الْغُصُونِ مِنَ الْشَّجَرْ
ወይም የጥበቃ ክልሉ ርግቦች እስካንጎራጎሩ
በዛፎች ቅርንጫፎች ላይ ሆነው