يَا وَاهِبَ الْإِنْسَانِ أَسْبَابَ الْهُدَى
ለሰው ልጅ የመመሪያ መንገዶችን የለገስክ ሆይ
Am
يَا وَاهِبَ الْإِنْسَانِ أَسْبَابَ الْهُدَى
يَا مَنْ بِحَمْدِ الْعَالَمِينَ تَفَرَّدَا
ለሰው ልጅ የቅን መንገድን ሰበቦች የለገስህ ሆይ
በዓለማት ምስጋና ብቻህን የተለየህ ሆይ
لِي عِنْدَ بَابِكَ يَا إِلَهِي دَعْوَةٌ
فِيهَا رَجَاءُ الْعُمْرِ جَاءَ مُجَسَّدَا
አምላኬ ሆይ! በደጅህ አንዲት ልመና አለችኝ
የሕይወት ዘመን ተስፋ አካል ለብሶ የቀረበባት
أَنْتَ الَّذِي مَا خَابَ عِنْدَكَ سَائِلٌ
أَيَكُونُ بَابُكَ دُونَ سُؤْلِي مُؤْصَدَا
አንተ ዘንድ ጠያቂ ፈጽሞ ተስፋ የማይቆርጥብህ ነህ
ታዲያ ደጅህ ከጥያቄዬ ፊት ተዘግቶ ይቀራልን?
فَبِفَضْلِكَ اللَّهُمَّ عِشْتُ مُوَحِّدا
أَيُرَدُّ عِنْدَكَ مَنْ أَتَاكَ مُوَحِّدَا
አላህ ሆይ! በችሮታህ አንድነትህን አጽንቼ ኖርኩ
አንድነትህን እየመሰከረ የመጣብህን ሰው ትመልሰዋለህን?
سُؤْلِي كَذَاتِكَ وَاحِدٌ فَبِحَقِّهَا
لَوْ لَحْظَةً دَعْنِي أُشَاهِدَ أَحْمَدَا
ልመናዬ እንደ ማንነትህ አንዲት ናት፤ እናም በዚሁ ሐቅ
ለአፍታም ቢሆን አህመድን እንዳየው ፍቀድልኝ