بُورِكْتِ يَا أُمَّ الْحَسَنَيْن
ቡርክት ነሽ የሐሰንና የሁሴን እናት ሆይ
Am
بُورِكْتِ يَا أُمَّ الْحَسَنَيْن
يَا فَاطِمَةْ الْزَّهْرَاءْ
የሁለቱ ሀሰኖች እናት ሆይ ተባረኪ
ፋጢማ አል-ዘህራ ሆይ
يَا آمِنَةْ يَا أُمَّ الزَّيْنْ
يَا حَامِلَةْ الْبُشْرَى
አሚና ሆይ የውቡ እናት
የምስራችን የተሸከምሽው
وَالسِّتِّ زَيْنَبْ نُورِ الْعَيْنْ
وَخَدِيجَةَ الْكُبْرَى
እመቤታችን ዘይነብ የዐይን ብርሃን
ታላቋ ኸዲጃም
صَلُّوا عَلَى عَبْدِ اللهْ
مَنْ قَدْ أَتَى بِكِتَابِ اللهْ
በአላህ ባሪያ ላይ ሰለዋት አውርዱ
የአላህን መጽሐፍ ይዞ በመጣው ላይ
وَمَنْ بِهِ قَدْ أَسْرَى اللهْ
سُبْحَانَ مَنْ أَسْرَى
አላህ በሌሊት ባስጓዘው ላይ
በሌሊት ላስጓዘው ጌታ ጥራት ይገባው
صَلُّوا عَلَى صَحْبِ الْمُخْتَارْ
رَسُولِنَا الْأَعْظَمْ
በተመረጠው ባልደረቦች ላይ ሰለዋት አውርዱ
በታላቁ መልእክተኛችን ላይ
حَيُّوا عَليٍ خَيْرَ الْأَبْرَارْ
إِمَامَنَا الْأَكْرَمْ
የደጎች በላጭ ለሆነው ለአሊ ሰላም በሉ
ለተከበረው ኢማማችን
وَعَلَى الْحُسَيْنْ نُورِ الْأَنْوَارْ
يَا سَعْدَ مَنْ سَلَّمْ
በብርሃናት ብርሃን በሆነው በሁሰይን ላይ
ሰላምታ ለሚያቀርብለት ሰው ምንኛ መታደል ነው
يَا أَهْلَ بَيْتِ الْمُصْطَفَى
عَلَيْكُمْ اَلْسَّلَامْ
የሙስጠፋ ቤተሰቦች ሆይ
ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን
أَهْلَ الْأَمَانَةْ وَالْوَفَا
وَالْخَيْرِ وَالْإِكْرَامْ
የታማኝነትና የቃል ኪዳን ሰዎች
የበጎነትና የልግስና ባለቤቶች