Am
صَلَاةُ اللّٰه سَلَامُ اللّٰه
عَلَىٰ طٰهٰ رَسُولِ اللّٰه
የአላህ ሶላት የአላህ ሰላም
በጣሀ የአላህ መልእክተኛ ላይ ይሁን
صَلَاةُ اللّٰه سَلَامُ الله
عَلَىٰ يٰسٓ حَبِيبِ الله
የአላህ ሶላት የአላህ ሰላም
በያሲን የአላህ ተወዳጅ ላይ ይሁን
تَوَسَّلْنَا بِبِسْمِ الله
وَبِالْهَادِي رَسُولِ الله
በአላህ ስም ተማጸንን
በመሪውና በአላህ መልእክተኛም
وَكُلِّ مُجَاهِدٍ لِلّٰه
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ለአላህ ብሎ በሚታገል ሁሉ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
إِلَهِي سَلِّمِ الْأُمَّةْ
مِنَ الْآفَاتِ وَالنِّقْمَةْ
አምላኬ ሆይ ኡመቱን አድን
ከጥፋቶችና ከመቅሰፍት
وَمِنْ هَمٍّ وَمِنْ غُمَّةْ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ከጭንቀትና ከሃዘንም
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
إِلَهِي نَجِّنَا وَاكْشِفْ
جَمِيعَ أَذِيَّةٍ وَاصْرِفْ
አምላኬ ሆይ አውጣን ግለጥልንም
ሁሉንም ችግርና አስወግድልን
مَكَائِدَ الْعِدَا وَالْطُفْ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
የጠላቶችን ተንኮልና እዘንልን
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
إِلَهِي نَفِّسِ الْكُرَبَا
مِنَ الْعَاصِينَ وَالْعَطْبَا
አምላኬ ሆይ ጭንቀትን አስወግድ
ከዓመፀኞችና ከጠፊዎች
وَكُلِّ بَلِيَّةٍ وَوَبَا
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ከእያንዳንዱ መከራና ወረርሽኝ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
فَكَمْ مِنْ رَحْمَةٍ حَصَلَتْ
وَكَمْ مِنْ ذِلَّةٍ فَصَلَتْ
ስንት እዝነት ተገኘ
ስንት ውርደትስ ተወገደ
وَكَمْ مِنْ نِعْمَةٍ وَصَلَتْ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ስንት ጸጋስ ደረሰ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
وَكَمْ أَغْنَيْتَ ذَا الْعُمْرِ
وَكَمْ أَوْلَيْتَ ذَا الْفَقْرِ
ስንት ባለእድሜን አበለጸግክ
ስንት ድሃንስ ረዳህ
وَكَمْ عَافَيْتَ ذَا الْوِزْرِ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ስንት ኃጢአተኛንስ አዳንክ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
لَقَدْ ضَاقَتْ عَلَى الْقَلْبِ
جَمِيعَ الْاَرْضِ مَعَ رَحْبِ
በእርግጥም በልባችን ላይ ጠበበች
ምድር ሁሉ ከስፋቷ ጋር
فَانْجُ مِنَ الْبَلَا الصَّعْبِ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ከከባድ መከራም አድነን
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
أَتَيْنَا طَالِبِي الرِّفْقِ
وَجُلِّ الْخَيْرِ وَالسَّعْدِ
ርህራሄን ፈልገን መጣን
ታላቅ መልካም ነገርንና ደስታን
فَوَسِّعْ مِنْحَةَ الْأَيْدِي
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
የእጆቻችንን ስጦታ አስፋልን
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
فَلَا تَرْدُدْ مَعَ الْخَيْبَةْ
بَلِ اجْعَلْنَا عَلَى الطَّيْبَةْ
በውድቀት አትመልሰን
ይልቁንም በመልካምነት ላይ አድርገን
أَيَا ذَا الْعِزِّ وَالْهَيْبَةْ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
የልዕልናና የግርማዊነት ባለቤት ሆይ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
وَإِنْ تَرْدُدْ فَمَنْ نَأْتِي
بِنَيْلِ جَمِيعِ حَاجَاتِي
ካባረርከን ወደ ማን እንሄዳለን
ፍላጎቶቻችንን ሁሉ ለማግኘት
أَيَا جَالِي الْمُلِمَّاتِ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا الله
ጭንቀቶችን አስወጋጅ ሆይ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
إِلَهِي أَغْفِرْ وَأَكْرِمْنَا
بِنَيْلِ مَطَالِبٍ مِنَّا
አምላኬ ሆይ ማረን አክብረንም
ፍላጎቶቻችንን በመስጠት
وَدَفْعِ مَسَاءَةٍ عَنَّا
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا اَللّٰه
ክፉ ነገርንም ከእኛ በመመለስ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
إِلَهِي أَنْتَ ذُو لُطْفٍ
وَ ذُو فَضْلٍ وَ ذُو عَطْفٍ
አምላኬ ሆይ አንተ የርህራሄ ባለቤት ነህ
የቸርነትና የጥበቃ ባለቤት
وَكَمْ مِنْ كُرْبَةٍ تَنْفِي
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا اَللّٰه
ስንት ጭንቀትንም ታስወግዳለህ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!
وَصَلِّ عَلَى النَّبِي الْبَرِّ
بِلَا عَدٍّ وَلَا حَصْرٍ
በደጉ ነቢይ ላይ ሶላት አውርድ
ያለ ቁጥርና ያለ ገደብ
وَآلِ سَادَةٍ غُرٍّ
بِأَهْلِ الْبَدْرِ يَا اَللّٰه
በክቡራን ቤተሰቦቻቸውም ላይ
በበድር ሰሃባዎች አማካኝነት አላህ ሆይ!