الْمُزْدَوِجَةُ الْحَسْنَاءُ فِي الْاِسْتِغَاثَةِ بِأَسْمَاءِ اللهِ الْحُسْنَى
በአላህ ውብ ስሞች በመማጸን ረገድ የቀረበችው ውቧ ድርብ ግጥም
Am
الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي تَحَمَّدَا
كَلَّمَ مُوسَى وَاصْطَفَى مُحَمَّدَا
ምስጋና ለአላህ ይሁን ራሱን ላመሰገነው
ሙሳን ላናገረው ሙሐመድን ለመረጠው
ثُمَّ الْصَّلَاةُ وَالْسَّلَامُ تُهْتَدَى
لِخَيْرِ مُرْسَلٍ هَدَى وَسَدَّدَا
ከዚያም ሰላትና ሰላም ይውረድ
መመሪያን ለሰጠውና ላቀናው ምርጥ መልክተኛ
وَالْآلِ وَالْصَّحْبِ وَمَنْ يَهْدِينَا
በቤተሰቦቹ፣ በባልደረቦቹና እኛን በሚመሩት ላይ
بِاسْمِ الْإِلَهِ وَبِهِ بَدِينَا
وَلَوْ عَبَدْنَا غَيْرَهُ شَقِينَا
በአምላክ ስም በእርሱም ጀመርን
ከእርሱ ውጪ ብናመልክ ኖሮ ተረገምን
يَا حَبَّذَا رَبًّا وَحَبَّ وَدِينَا
وَحَبَّذَا مُحَمَّدٌ هَادِينَا
ምንኛ ያማረ ጌታ፣ ውዴታና ሃይማኖት
ምንኛ ያማረ መሪያችን ሙሐመድ
لَوْلَاهُ مَا كُنَّا وَلَا بَقِينَا
እርሱ ባይኖር ኖሮ ባልኖርንና ባልቀረንም ነበር
الْلَّهُمَّ لَوْلَا أَنْتَ مَا اهْتَدَيْنَا
وَلَا تَصَدَّقْنَا وَلَا صَلَّيْنَا
አላህ ሆይ! አንተ ባትኖር ኖሮ ባልተመራን ነበር
ሰደቃም ባልሰጠንና ባልሰገድንም ነበር
فَأَنْزِلَنْ سَكِينَةً عَلَيْنَا
وَثَبِّتِ الْأَقْدَامَ إِنْ لَا قَيْنَا
እርጋታን በእኛ ላይ አውርድ
ጠላትን ስንገጥምም እርምጃችንን አጽናልን
نَحْنُ الْأُ لَى جَاؤُوكَ مُسْلِمِينَا
እኛ ሙስሊሞች ሆነን ወደ አንተ የመጣን ቀዳሚዎች ነን
وَالْمُشْرِكُونَ قَدْ بَغَوْا عَلَيْنَا
إِذَا أَرَادُوا فِتْنَةً أَبَيْنَا
አጋሪዎች በእኛ ላይ ወሰን ተሻገሩ
ፈተናን በፈለጉ ጊዜ እምቢ አልን
وَقَدْ تَدَاعَى جَمْعُهُمْ عَلَيْنَا
طِبْقَ الْأَحَادِيثَ الَّتِي رَوَيْنَا
ስብስባቸው በእኛ ላይ ተጠራርቷል
በዘገብናቸው ሐዲሶች መሠረት
فَارْدُدْهُمُ الْلَّهُمَّ خَاسِرِينَ
አላህ ሆይ! ከሳሪዎች አድርገህ መልሳቸው
اللَّهُ يَا رَحْمَنُ يَا رَحِيمُ
اللَّهُ يَا حَيُّ وَيَا قَيُّومُ
አላህ ሆይ! አንተ ራሕማን አንተ ራሒም
አላህ ሆይ! አንተ ሕያው አንተ ቀዩም
اللَّهُ يَا قَوِيُّ يَا قَدِيمُ
اللَّهُ يَا عَلِيُّ يَا عَظِيمُ
አላህ ሆይ! አንተ ብርቱ አንተ ቀዳሚ
አላህ ሆይ! አንተ ልዑል አንተ ታላቅ
لَا يَنْبَغِي لِلْظُّلْمِ أَنْ يَعْلُونَا
በደል በእኛ ላይ ሊሰለጥን አይገባም
اللَّهُ يَا لَطِيفُ يَا عَلِيمُ
اللَّهُ يَا رَؤُوفُ يَا حَكِيمُ
አላህ ሆይ! አንተ ረቂቅ አንተ አዋቂ
አላህ ሆይ! አንተ ርኅሩኅ አንተ ጥበበኛ
اللَّهُ يَا تَوَّابُ يَا حَلِيمُ
اللَّهُ يَا وَهَّابُ يَا كَرِيمُ
አላህ ሆይ! አንተ ተውባን ተቀባይ አንተ ታጋሽ
አላህ ሆይ! አንተ ሰጪ አንተ ቸር
هَبْنَا الْعُلَا وَاجْعَلْ عِدَانَا الْدُّونَا
ልዕልናን ስጠን ጠላቶቻችንንም ዝቅ አድርጋቸው
اللَّهُ يَا مَالِكُ يَا مُنِيرُ
اللَّهُ يَا مَلِيكُ يَا قَدِيرُ
አላህ ሆይ! አንተ ባለቤት አንተ አብሪ
አላህ ሆይ! አንተ ንጉሥ አንተ ቻይ
اللَّهُ يَا مَوْلَى وَيَا نَصِيرُ
اللَّهُ أَنْتَ الْمَلِكُ الْكَبِيرُ
አላህ ሆይ! አንተ ረዳት አንተ ደጋፊ
አላህ ሆይ! አንተ ታላቁ ንጉሥ ነህ
لَيْسَ عِدَانَا لَكَ مُعْجِزِينَا
ጠላቶቻችን አንተን አያቅቱህም
اللَّهُ يَا شَاكِرُ يَا شَكُورُ
اللَّهُ يَا عَفُوُّ يَا غَفُورُ
አላህ ሆይ! አንተ አመስጋኝ አንተ ምስጋናን ተቀባይ
አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ አንተ መሐሪ
اللَّهُ يَا عَالِمُ يَا خَبِيرُ
اللَّهُ يَا فَتَّاحُ يَا بَصِيرُ
አላህ ሆይ! አንተ አዋቂ አንተ ዘጋቢ
አላህ ሆይ! አንተ ከፋች አንተ ተመልካች
لَا تَحْرِمْنَا فَتْحَكَ الْمُبِينَا
ግልጽ የሆነውን ድልህን አትንፈገን
اللَّهُ يَا ظَاهِرُ يَا جَلِيلُ
اللَّهُ يَا بَاطِنُ يَا وَكِيلُ
አላህ ሆይ! አንተ ግልጽ አንተ ግርማዊ
አላህ ሆይ! አንተ ስውር አንተ መከታ
اللَّهُ يَا صَادِقُ يَا جَمِيلُ
اللَّهُ يَا حَافِظُ يَا كَفِيلُ
አላህ ሆይ! አንተ እውነተኛ አንተ ውብ
አላህ ሆይ! አንተ ጠባቂ አንተ ዋስ
كُنْ حَافِظًا لَنَا وَكُنْ مُعِينَا
ለእኛ ጠባቂና ረዳት ሁንልን
اللَّهُ يَا غَنِيُّ يَا حَمِيدُ
اللَّهُ يَا مُغْنِي وَيَا رَشِيدُ
አላህ ሆይ! አንተ ሀብታም አንተ ምስጉን
አላህ ሆይ! አንተ አበልጻጊ አንተ መሪ
اللَّهُ يَا مُبْدِئُ يَا مُعِيدُ
اللَّهُ يَا عَزِيزُ يَا مَجِيدُ
አላህ ሆይ! አንተ ጀማሪ አንተ መላሽ
አላህ ሆይ! አንተ አሸናፊ አንተ የተከበርክ
لِعِزِّكَ الْتَّوْحِيدُ يَشْكُو الْهُوْنَا
ለክብርህ ሲል ተውሒድ ውርደትን ያወሳል
اللَّهُ يَا قَادِرُ يَا مُقْتَدِرُ
اللَّهُ يَا قَاهِرُ يَا مُؤَخِّرُ
አላህ ሆይ! አንተ ቻይ አንተ አሸናፊ
አላህ ሆይ! አንተ ገዢ አንተ አቆይ
اللَّهُ يَا فَاطِرُ يَا مُصَوِّرُ
اللَّهُ يَا مُحْصِي وَيَا مُدَبِّرُ
አላህ ሆይ! አንተ ፈጣሪ አንተ ቀራጭ
አላህ ሆይ! አንተ ቆጣሪ አንተ አስተዳዳሪ
دَبِّرْ لَنَا وَدَمِّرِ الْعَادِينَا
ለእኛ አብጅልን በደለኞችንም አጥፋልን
اللَّهُ يَا دَائِمُ لَا يَمُوتُ
اللَّهُ يَا قَائِمُ لَا يَفُوتُ
አላህ ሆይ! አንተ ዘላቂ የማይሞት
አላህ ሆይ! አንተ ቋሚ የማይዘነጋ
اللَّهُ يَا مُحْيِي وَيَا مُمِيتُ
اللَّهُ يَا مُغِيثُ يَا مُقِيتُ
አላህ ሆይ! አንተ ሕይወት ሰጪ አንተ ገዳይ
አላህ ሆይ! አንተ ደራሽ አንተ ቀላቢ
كُنْ غَوْثَنَا وَحِصْنَنَا الْحَصِينَا
ረዳታችንና ጠንካራ ምሽጋችን ሁንልን
اللَّهُ يَا بَاسِطُ أَنْتَ الْوَاسِعُ
اللَّهُ يَا قَابِضُ أَنْتَ الْمَانِعُ
አላህ ሆይ! አንተ ዘርጊ ሰፊው ነህ
አላህ ሆይ! አንተ ጨባጭ ከልካዩ ነህ
اللَّهُ يَا خَالِقُ أَنْتَ الْجَامِعُ
اللَّهُ يَا خَافِضُ أَنْتَ الْرَّافِعُ
አላህ ሆይ! አንተ ፈጣሪ ሰብሳቢው ነህ
አላህ ሆይ! አንተ አዋራጅ ከፍ አድራጊው ነህ
اِرْفَعْ مَعَالِينَا لِعِلِّيِّينَا
ደረጃችንን ወደ ከፍተኛው እርከን አውጣልን
اللَّهُ ذُو الْمَعَارِجِ الْرَّفِيعُ
اللَّهُ يَا وَافِي وَيَا سَرِيعُ
አላህ ሆይ! የከፍታ መንገዶች ባለቤት
አላህ ሆይ! አንተ ታማኝ አንተ ፈጣን
اللَّهُ يَا كَافِي وَيَا سَمِيعُ
يَا نُورُ يَا هَادِي وَيَا بَدِيعُ
አላህ ሆይ! አንተ በቂ አንተ ሰሚ
አንተ ብርሃን መሪና አስገኝ
أَدَّبْتَنَا بِمَا جَرَى يَكْفِينَا
በሆነው ነገር ገሠጽከን እርሱም ይበቃናል
اللَّهُ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ
اللَّهُ ذُو الْطَّوْلِ عَلَى الْدَّوَامِ
አላህ ሆይ! የግርማና የክብር ባለቤት
አላህ ሆይ! የችሮታ ባለቤት ለዘላለም
اللَّهُ يَا ذَا الْفَضْلِ وَالْإِنْعَامِ
وَالْسَّيِّدُ الْمِطْلَقُ لِلْأَنَامِ
አላህ ሆይ! የጸጋና የልግስና ባለቤት
የፍጡራን ሁሉ ፍጹም ጌታ
ارْحَمْ عَبَيْدًا لَكَ عَابِدِينَا
አንተን የሚያመልኩ ደካማ ባሮችህን እዘንላቸው
اللَّهُ يَا أَوَّلُ أَنْتَ الْوَاحِدُ
اللَّهُ يَا آخِرُ أَنْتَ الْرَّاشِدُ
አላህ ሆይ! አንተ ቀዳሚው አንዱ ነህ
አላህ ሆይ! አንተ መጨረሻው መሪው ነህ
يَا وِتْرُ يَا مُتَكَبِّرُ يَا وَاجِدُ
يَا بَرُّ يَا مُتَفَضِّلُ يَا مَاجِدُ
አንተ ነጠላ ኩሩና አግኝ
አንተ ቸር ባለጸጋና የላቅክ
بِفَضْلِكَ اقْبَلْنَا عَلَى مَا فِينَا
በችሮታህ ባለንበት ሁኔታ ተቀበለን
اللَّهُ يَا مُبِينُ يَا وَدُودُ
اللَّهُ يَا مُحِيطُ يَا شَهِيدُ
አላህ ሆይ! አንተ ግልጽ አንተ ተወዳጅ
አላህ ሆይ! አንተ ከባቢ አንተ ምስክር
اللَّهُ يَا مَتِينُ يَا شَدِيدُ
يَا مَنْ هُوَ الْفَعَّالُ مَا يُرِيدُ
አላህ ሆይ! አንተ ጽኑ አንተ ብርቱ
አንተ የፈለግከውን አድራጊ የሆንክ
إِنَّا ضِعَافٌ لَكَ قَدْ لَجِينَا
እኛ ደካሞች ነን ወደ አንተ ተጠግተናል
اللَّهُ يَا مُعِزُّ يَا مُقَدِّمُ
اللَّهُ يَا مُذِلُّ يَا مُنْتَقِمُ
አላህ ሆይ! አንተ አክባሪ አንተ አስቀዳሚ
አላህ ሆይ! አንተ አዋራጅ አንተ ተበቃይ
الْبَادِئُ الْبَاقِي فَلَا يَنْعَدِمُ
الْمُحْسِنُ الْوَالِي الْحَفِيظُ الْأَكْرَمُ
ጀማሪውና የማይጠፋው ዘላቂ
በጎ አድራጊው ገዢው ጠባቂውና ምርጡ
ليسَ لَنَا سِوَاكَ مَنْ يَحْمِينَا
ከአንተ ውጭ የሚጠብቀን ማንም የለንም
اللَّهُ يَا وَارِثُ أَنْتَ الْأَبَدُ
اللَّهُ يَا بَاعِثُ أَنْتَ الْأَحَدُ
አላህ ሆይ! አንተ ወራሽ ዘላለማዊው ነህ
አላህ ሆይ! አንተ ቀስቃሽ አንዱ ነህ
يَا مَالِكَ الْمُلْكِ الْإِلَهُ الْصَّمَدُ
لَا كُفُوءٌ لَا وَالِدٌ لَا وَلَدُ
የንግሥና ባለቤት የተብቃቃህ አምላክ
አምሳያ የሌለህ ወላጅም ተወላጅም የሌለህ
كُفَّ الْعِدَا عَنَّا فَقَدْ أُوذِينَا
ጠላቶችን ከእኛ ከልክልልን ተጎድተናልና
اللَّهُ يَا غَالِبُ يَا قَهَّارُ
اللَّهُ يَا نَافِعُ أَنْتَ الْضَّارُّ
አላህ ሆይ! አንተ አሸናፊ አንተ ገዢ
አላህ ሆይ! አንተ ጠቃሚ ጎጂውም አንተ ነህ
اللَّهُ يَا بَارِئُ يَا غَفَّارُ
يَا رَبُّ يَا ذَا الْقُوَّةِ الْجَبَّارُ
አላህ ሆይ! አንተ ፈጣሪ አንተ መሐሪ
ጌታ ሆይ! የኃይል ባለቤትና ግዳጅ ፈጻሚ
قَوِّمْ لَنَا الْدُّنْيَا وَقَوِّ الْدِّينَا
ዱንያችንን አቅናልን ዲናችንንም አጠናክረን
اللَّهُ رَبُّ الْعِزَّةِ الْسَّلَامُ
الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَلَّامُ
አላህ ሆይ! የክብር ጌታ ሰላም
እምነት ሰጪው ተቆጣጣሪውና አዋቂው
ذُو الْرَّحْمَةِ الْأَعْلَى الْأَعَزُّ التَّامُّ
مَنْ دِينُهُ الْحَقُّ هُوَ الْإِسْلَامُ
የራሕመት ባለቤት ልዑሉ ብርቱው ሙሉው
ሃይማኖቱ እውነት የሆነው እርሱ ኢስላም ነው
قَيِّضْ لَهُ الْلَّهُمَّ نَاصِرِينَا
አላህ ሆይ! ለእርሱ ረዳቶችን መድብለት
اللَّهُ أَنْتَ الْمُتَعَالِي الْحَكَمُ
الْفَرْدُ ذُو الْعَرْشِ الْوَلِيُّ الْأَحْكَمُ
አላህ ሆይ! አንተ ልዑል ፈራጅ
ብቸኛው የዐርሽ ባለቤት ጠባቂውና ጥበበኛው
الْغَافِرُ الْمُعْطِي الْجَوَادُ الْمُنْعِمُ
الْعَادِلُ الْعَدْلُ الْصَّبُورُ الْأَرْحَمُ
መሐሪው ሰጪው ቸሩና ለጋሱ
ፍትሐዊው ፍትሕ ታጋሹና አዛኙ
مَكِّنْ لَنَا فِي أَرْضِنَا تَمْكِينَا
በምድራችን ላይ ጽናትን አጎናጽፈን
اللَّهُ يَا قُدُّوسُ يَا بُرْهَانُ
يَا بَرُّ يَا حَنَّانُ يَا مَنَّانُ
አላህ ሆይ! አንተ ቅዱስ አንተ ማስረጃ
አንተ ቸር አዛኝና ለጋስ
يَا حَقُّ يَا مُقْسِطُ يَا دَيَّانُ
تَبَارَكَتْ أَسْمَاؤُكَ الْحِسَانُ
አንተ እውነት ፍትሐዊና ዳኛ
ያማሩት ስሞችህ የተባረኩ ናቸው
بِهَا قَرَعْنَا بَابَكَ الْمَصُونَا
በእነርሱ የተጠበቀውን ደጃፍህን አንኳኳን
اللَّهُ يَا خَلَّاقُ يَا مُنِيبُ
اللَّهُ يَا رَزَّاقُ يَا حَسِيبُ
አላህ ሆይ! አንተ ፈጣሪ አንተ መላሽ
አላህ ሆይ! አንተ ሲሳይ ሰጪ አንተ ተቆጣጣሪ
اللَّهُ يَا قَرِيبُ يَا رَقِيبُ
الْمُسْتَعَانُ الْسَّامِعُ الْمُجِيبُ
አላህ ሆይ! አንተ ቅርብ አንተ ተመልካች
ታላቁ ረዳት ሰሚውና ምላሽ ሰጪው
إِنَّا دَعَوْنَاكَ اسْتَجِبْ آمِينَا
በእርግጥ ጠርተንሃልና አሜን ብለህ ተቀበለን