اَلْهِجْرَةُ رِحْلَةُ هَادِيْنَا
ሂጅራ የመሪያችን ጉዞ ነው።
Am
اَلْهِجْرَةُ رِحْلَةُ هَادِيْنَا
حَمَلَ الْإِسْلَامَ لَنَا دِيْنَا
ሂጅራ የመሪያችን ጉዞ ናት
እስልምናን ሃይማኖታችን አድርጎ አመጣልን
فَسَلَامُ اللّٰهِ عَلَی الْهَادِيْ
وَالْكَوْنُ يُرَدِّدُ آمِيْنَا
የአላህ ሰላም በመሪው ላይ ይሁን
ፍጥረተ ዓለሙም "አሚን" እያለ ያስተጋባል
رَحَلَ الْصِّدِّيقُ عَنِ الْدَّارِ
فِی صَحْبَةِ خَيْرِ الْأَبْرَارِ
ሲዲቅ ከቤቱ ተለይቶ ወጣ
ከደጋጎች ሁሉ በላጭ ጋር በመሆን
صَلَوَاتُ اللّٓهِ تُبَارِکُهُ
مَلَأَ الْدُّنْيَا بِالْأَنْوَارِ
የአላህ በረከት በእርሱ ላይ ይሁን
ዓለምን በብርሃናት ሞልቷታልና
اَللّٰهُ تَكَفَّلَ يَحْمِيْهِ
وَعَلِيٌّ أَصْبَحَ يَفْدِيْهِ
አላህ እሱን መጠበቅን ተረከበ
ዓሊይም ለርሱ ራሱን መስዋዕት አደረገ
وَبِسِرِّ الْقَوْمِ الْأَشْرَارِ
بِنْتُ الْصِّدِّيْقِ تُوَافِيْهِ
የክፉዎችን ወገኖች ምስጢር ይዛ
የሲዲቅ ልጅ ትገናኘው ነበር
وَصَلَ الْمُخْتَارُ إِلَی طَيْبَةْ
وَ الْكُفْرُ تَرَاجَع فِی خَيْبَةْ
ሙክታር ጠይባህ ደረሱ
ክህደትም በውርደት ወደ ኋላ አፈገፈገ
وَ جُنُوْدُ اللّٰهِ تُحِيْطُ بِهِ
مِنْ نُوْرِ الْاِسْلَامِ الْهَيْبَة
የአላህ ሰራዊት ከበቡት
ከእስልምና ብርሃን በሆነ ግርማ
بِالْرُّوْحِ سَنَحْمِی الْمُخْتَارا
وَ نُقَاتِلْ عَنْهُ الْكُفَّارا
በነፍሳችን ሙክታርን እንጠብቃለን
ስለ እርሱም ከከሃዲዎች ጋር እንዋጋለን
عَهْدًا لِلّٰـهِ نُبَايِعُهُ
جُنْدًا لِلّٰـهِ وَ اَنْصَارا
ለአላህ ቃል ኪዳን እንገባለን
የአላህ ሰራዊትና ረዳቶች ሆነን