هَذَا الْمَقَامُ الَّذِي لَاذَتْ بِهِ الْأُمَمُ
ይህ አሕዛብ የተጠለሉበት ማዕረግ ነው።
Am
هَذَا الْمَقَامُ الَّذِي لَاذَتْ بِهِ الْأُمَمُ
وَأَذْعَنَتْ لِعُلَاهُ الْعُرْبُ وَالْعَجَمُ
ይህ ህዝቦች የተጠለሉበት ማዕረግ ነው
አረብም ይሁን የውጭ ህዝብ ለልዕልናው የታዘዘለት
هَذَا مَقَامُ رَسُولِ اللَّهْ أَكْرَمُ مَنْ
جَاءَتْهُ مِنْ رَبِّهِ الْأَحْكَامُ وَالْحِكَمُ
ይህ የላቁት የፈጣሪ መልክተኛ ማዕረግ ነው
ከጌታቸው ዘንድ ህግጋትና ጥበብ የመጡላቸው
هَذَا مُحَمَّدُ الْهَادِي الَّذِي مُحِيَتْ
عَنَّا بِنُورِ هُدَاهُ الْظُّلْمُ وَ الْظُّلَمُ
ይህ መሪው ሙሐመድ ነው
በቅን መመሪያው ብርሃን ግፍና ጨለማ ከእኛ ላይ የተወገዱበት
هَذَا الَّذِي قَدْ سَمَا فَوْقَ الْسَّمَا
إِلَى مَقَامِ عِزٍّ تَنَاهَتْ دُونَهُ الْأُمَمُ
ይህ ከሰማያት በላይ የላቀ ነው
ህዝቦች ሊደርሱበት ወደማይችሉት የክብር ማዕረግ
يَا سَيِّدِي يَا رَسُولَ اللَّهْ يَا أَمَلِي
يَا مَنْ أَلُوذُ بِهِ إِنْ زَلَّتِ الْقَدَمُ
ጌታዬ ሆይ! የፈጣሪ መልክተኛ ሆይ! ተስፋዬ ሆይ!
እግሬ በሚንሸራተትበት ጊዜ የምጠለልብህ
بِكَ اهْتَدَيْتُ إِلَى الْإِيمَانِ فَاتَّصَلَتْ
بِذَاكَ عِنْدِي مِنْ أَفْضَالِكَ الْنِّعَمُ
ባንተ አማካኝነት ወደ እምነት ተመራሁ
ከችሮታህም የተነሳ ጸጋዎች በእኔ ላይ ተከታተሉ
صَلَّى عَلَيْكَ إِلَهُ الْخَلْقِ مَا سَجَعَتْ
وَرْقٌ وَمَا هَطَلَتْ مِنْ سُحْبِهَا دِيَمُ
የፍጡራን አምላክ ሰላቱን ያውርድብህ፤ ርግብ ባዜመች ቁጥር
ከደመናዎችም ዝናብ በፈሰሰ ቁጥር