شَهْرُ الرَّبِيع وَافَانَا
The Month of Rabiʿ Is Upon Us
Am
Am
شَهْرُ الرَّبِيع وَافَانَا
أَقْبَلْ عَلَيْنَا وَهَنَّانَا
የረቢዕ ወር መጣልን
ወደ እኛ ቀርቦ አስደሰተን
بِهِ أَتَانَا رَسُولُ الله
لِلدِّينِ حَقًّا هَدَانَا
በእርሱም የአላህ መልእክተኛ መጡ
ወደ ሃይማኖቱ በእውነት መሩን
شَهْرٌ بِهِ جَاءَ الرَّسُولْ
الْهَاشِمِي بَابُ الْوُصُولْ
መልእክተኛው የመጡበት ወር
ያ ሃሺሚያዊው የመድረሻ በር
بِقُدُومِهِ نِلْنَا الْقَبُولْ
سُبْحَانَ مَنْ قَدْ أَعْطَانَا
በመምጣታቸው ተቀባይነትን አገኘን
ይህን የለገሰን ጌታ ጥራት ይገባው
شَهْرٌ بِهِ نِلْنَا الْهُدَىٰ
وَبِهِ انْجَلَى عَنَّا الرَّدَى
ቅኑን መንገድ ያገኘንበት ወር
ጥፋትም ከእኛ የተወገደበት
بِجَمَالِهِ لَمَّا بَدَى
مِنْ كُلِّ خَطْبٍ نَجَّانَا
ውበታቸው በታየ ጊዜ
ከጭንቀት ሁሉ አዳነን
يَا رَبِّ صَلِّ يَا سَلَامْ
عَلَى النَّبِي مَاحِي الظَّلَامْ
ጌታዬ ሆይ ሰላምን አውርድ
ጨለማውን በሚያጠፉት ነቢይ ላይ
وَالْآلِ وَالصَّحْبِ الْكِرَامْ
مَا فِيْهِ شَادٍ غَنَّانَا
በቤተሰቦቻቸውና ክቡር ባልደረቦቻቸው ላይ
አወድሷቸው በሚዘመርበት ሁሉ