طَابَ لِي خَلْعُ عِذَارِي
My Wantonness Befits Me
Am
طَابَ لِي خَلْعُ عِذَارِي
فِي هَوَى الْبَدْرِ الْتَّمَامْ
ልጓሜን መጣሌ ይስማማኛል
ሙሉ ጨረቃ ለሆነው ፍቅሬ
بِافْتِقَارِي وَانْكِسَارِي
أَرْتَجِيْ نَيْلَ الْمَرَامْ
በችጋሬና በስብራቴ
የምሻውን ግብ ለማግኘት ተስፋ አደርጋለሁ
يَا عَذُوْلِي لَا تَلُمْنِي
مَا عَلَى الْعَاشِقُ مَلَامْ
አንተ ወቃሿ ሆይ አትውቀሰኝ
በአፍቃሪ ላይ ምንም ወቀሳ የለበትምና
اُدْنُ مِنِّي وَارْوِ عَنِّيْ
أَنَا فِي الْعِشْقِ إِمَامْ
ወደ እኔ ቅረብ ከእኔም ተረክ
እኔ በፍቅር ጥበብ ውስጥ መሪ ነኝና
خَمْرَةُ الْأَحْبَابِ تُجْلَ
هِيَ حِلٌّ لَا حَرَامْ
የወዳጆች ወይን ይፈሳል
እርሱ የተፈቀደ እንጂ ክልክል አይደለም
مِنْ عُيُونِ الْعِيْنِ تُمْلَى
صَانَهَا الْبَرُّ الْسَّلَامْ
ከዐይነ-ርግብ ምንጮች ይቀዳል
ቸሩና ሰላም ሰጪው አምላክ ጠብቆታል
يَا أَخَا الْأَشْوَاقِ يَمِّمْ
سَيِّدَ الْرُّسْلِ الْكِرَامْ
አንተ የናፍቆት ወንድም ሆይ! አቅጣጫህን አድርግ
ወደተከበሩት መላክተኞች አለቃ
وَاغْنَمِ الْذِّكْرَ وَزَمْزِمْ
بِصَلَاةٍ مَعْ سَلَامْ
ዝክርን አትርፍና አንጎራጉር
በውዳሴና በሰላምታ
لِحَبِيْبِ الله أَحْمَدْ
كُلَّمَا جَنَّ الْظَّلَامْ
ለአላህ ተወዳጅ ለአሕመድ
የሌሊት ጨለማ በሰፈነ ቁጥር ሁሉ
كُلُّ مَنْ وَالَاهُ يَسْعَدْ
وَيَنَالْ حُسْنَ الْخِتَامْ
እርሱን የወደደ ሁሉ ይደሰታል
የመጨረሻውንም መልካም ፍጻሜ ያገኛል