اَلـلَّـهُ يَـا اَلـلَّـه صَـلَّـى عَـلَـى الـزَّيْـن
አላህ ያ አላህ በውቡ ላይ ሶላት ይውረድ
Am
اَلـلَّـهُ يَـا اَلـلَّـه
صَـلْـوا عَـلَـى الْـزَّيْـنِ
አላህ ሆይ ኦ አላህ
በዚያ ውብ ላይ ሰለዋት አውርዱ
طَـاطَـا الْـقَـمَـرْلِأَحْـمَـد
وَانْـشَـقَّ نِـصْـفَـيْـنِـى
ጨረቃ ለአህመድ ታዘዘች
በሁለትም ተሰነጠቀች
أَبُـو بَـكْـرُ يَـا صِـدِّيـقْ
صَـاحِـبِ الْـنَّـبِـى وَرَفِـيـق
አቡበክር ሆይ አንቱ እውነተኛ
የነቢዩ ባልደረባና የቅርብ ጓደኛ
بِرُوحُهْ فَدَاهْ فِي الضِّيقْ
مِـنْ لَـدْغَـةِ الْـنِّـيـنِـى
በጭንቅ ጊዜ በነፍሱ ተበጀው
ስለ እርሱም የእባብን ነክሻ ታገሰ
لَـمَّـا عُـمَـرْ أَسْـلَـم
فَـرِحَ الْـنَّـبِـى وَتَـبَـسَّـم
ኡመር በእስልምና በገባ ጊዜ
ነቢዩ ተደሰቱ ፈገግም አሉ
تَـبَـاشَـرَ الْإِسْـلَام
بِـدُخُـولِـهْ فِـي الْـدِّيـنِـى
እስልምናም የምስራች ተባባለ
ወደ ሃይማኖቱ በመግባቱ
عُـثْـمَـانُ يَـا عُـثْـمَـان
يَـا جَـامِـعَ الْـقُـرْءَان
ኡስማን ሆይ ኡስማን ሆይ
ቁርአንን የሰበሰብክ
صِـهْـرِ الْـنَّـبِـى الْـعَـدْنَـان
زَوَّجَـهُ بِـنْـتَـيْـنِـى
የዓድናኒው ነቢይ አማች
ሁለት ሴት ልጆቹን የዳረልህ
عَـلِـىُّ يَـا كَـرَّار
سَـيْـفُـكَ طَـوِيـل بَـتَّـار
አሊይ ሆይ አንቱ ጀግና ተዋጊ
ሰይፍህ ረጅም ነው ስለታም
يَـا هَـازِمَ الْـكُـفَّـار
قَـتَـلَ الْـمَـلَاعِـيـنِـى
የከሃዲያን ድል አድራጊ
እርጉም ጠላቶችን የገደልክ
جَـاتُـهْ الْـمُـرَبِّـيَـةْ
حَـلِـيـمَـةْ الْـسَّـعْـدِيَّـة
ሞግዚቱ መጣችለት
ሀሊማ አል-ሰዕዲያ
قَـالَـتْ وَهَـبُـوةْ لِـيَـا
يَـا رَبِّ هَـنِّـيـنِـى
አለችም "እርሱን ለእኔ ስጡኝ"
"ጌታዬ ሆይ በእርሱ አስደስተኝ"
جَـالُـه الْـجَـمَـل جَـالُـه
يَـزْحَـف عَـلَـى عِـقَـالُـه
ግመሉ ወደ እርሱ መጣ
በጠፍሩ ላይ እየተሳበ
لَـمَّـا جَـالُـه جَـمَـالُـه
سَـلِّـم عَـلَـى الـزَّيْـنِـى
ውበቱን ባየ ጊዜ
በዚያ ውብ ላይ ሰላምታ አቀረበ