حَيُّوا الْهَادِي بِأَجْمَلَ ذِكْرَى
መሪውን እጅግ ባማረ መታሰቢያ ሰላም በሉ::
Am
حَيُّوا الْهَادِي بِأَجْمَلَ ذِكْرَى
صَلُّوا مَعَنَا يَا حُضَّارْ
መሪውን በሚያምር ዝክሬ ሰላም በሉት
እናንተ በቦታው ያላችሁ ከእኛ ጋር ሶለዋት አውርዱ
فَهُوَ عِمَادِي يَوْمَ الْمَعَادِ
نَبِيُّنَا طٰهَ الْمُخْتَارْ
እርሱ ነው በትንሣኤ ቀን መደገፊያዬ
ነቢያችን ጧሃ የተመረጡት
صَلُّوا مَعَنَا
ከእኛ ጋር ሶለዋት አውርዱ
هٰذَا الَّذِي سَرَى لَيْلًا
ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّى
ይህ ነው በሌሊት የተጓዘው
ከዚያም የቀረበና የተጠጋው
وَهُوَ بِالْأُفُقِ الْأَعْلَى
حَبَاهُ الْوَاحِدُ الْسَّتَّارْ
እርሱም በላቀው አድማስ ላይ ሳለ
አንድዬው ነውር ሸፋኙ ችሮታውን ለገሰው
فَهُوَ عِمَادِي يَوْمَ الْمَعَادِ
نَبِيُّنَا طٰهَ الْمُخْتَارْ
እርሱ ነው በትንሣኤ ቀን መደገፊያዬ
ነቢያችን ጧሃ የተመረጡት
صَلُّوا مَعَنَا
ከእኛ ጋር ሶለዋት አውርዱ
عَلَى الْعَرْشِ رَقَى الْجَمِيلْ
وَكَلَّمَهُ الْمَوْلَى الْجَلِيلْ
ውቡ ወደ ዐርሽ ከፍ አለ
ግርማዊው ጌታም አነጋገረው
وَقَالَ أَبْشِرْ يَا خَلِيلْ
شَفَاعَتُكَ لِمَنْ تَخْتَارْ
"ወዳጄ ሆይ ተበሰር" አለው
"ምልጃህም ለመረጥኸው ሰው ነው"
فَهُوَ عِمَادِي يَوْمَ الْمَعَادِ
نَبِيُّنَا طٰهَ الْمُخْتَارْ
እርሱ ነው በትንሣኤ ቀን መደገፊያዬ
ነቢያችን ጧሃ የተመረጡት
صَلُّوا مَعَنَا
ከእኛ ጋር ሶለዋት አውርዱ
صَلَّى مَوْلَانَا عَلَيْهْ
وَالْآلِ وَالصَّحْبِ لَدَيْهْ
ጌታችን በእርሱ ላይ ሶለዋት ያውርድ
በቤተሰቦቹና በዙሪያው ባሉ ባልደረቦቹም ላይ
مَنْ جَاهَدُوا بَيْنَ يَدَيْهْ
وَنَوَّرُوا لَنَا الْأَفْكَارْ
በፊቱ የታገሉትና የቆሙት
አእምሯችንንም ያበሩልን
فَهُوَ عِمَادِي يَوْمَ الْمَعَادِ
نَبِيُّنَا طٰهَ الْمُخْتَارْ
እርሱ ነው በትንሣኤ ቀን መደገፊያዬ
ነቢያችን ጧሃ የተመረጡት
صَلُّوا مَعَنَا
ከእኛ ጋር ሶለዋት አውርዱ