وَاصَلُونِي بَعْدَ بُعْدِي
ከርቀቴ በኋላ አንድነትን ለገሱኝ
Am
وَاصَلُونِي بَعْدَ بُعْدِي
وَرَعُوا سَالِفَ عَهْدِي
ከራቅሁ በኋላ በውህደት መጡልኝ
የቀደመ ቃል ኪዳኔንም አከበሩልኝ
وَعلَى رَغْمِ الْحَسُودِ
أَنْجَزُوا بِالْوَصْلِ وَعْدِي
ምቀኛ ቢኖርም እንኳ
ቃላቸውን በውህደት ፈጸሙልኝ
يَا سُرُورْي بالَّتدَاني
يَا هَنَا حَظِّي وَسَعْدِي
በመቀራረባችን ሆይ ደስታዬ!
የእድሌና የደስታዬ እርካታ ሆይ!
جَادَ لِي بَدْرِي بِوَصْلِ
يا هَنَائِي نِلْتُ قَصْدِي
ሙሉ ጨረቃዬ በውህደት ቸረኝ
ደስታዬ ሆይ፤ ፍላጎቴን አሳካሁ
فَاجْتَمِعْ يَا مَاءَ عَيْني
وانْطَفِي يَا نَارَ وَجْدِي
የአይኔ እምባ ሆይ (በደስታ) ተሰብሰብ
የናፍቆቴም እሳት ሆይ ጥፋ
أَنَا فِي لَيْلَةِ أُنْسِي
قَدْ صَفَا مَوْرِدُ وِرْدِي
በወዳጅነት ሌሊቴ ውስጥ ነኝ
የመጠጥ ምንጬም ጥርት አለልኝ
وَتَناولْتُ كُؤُوسي
بَين رَيْحَانٍ وَوَرْدِ
ጽዋዎቼንም በእጄ ተቀበልኩ
በሬሃንና በጽጌረዳ መዓዛ መካከል
مِنْ يَدَيْ حُلْوِ الْتثَنيِّ
فَاتِنٍ أَهْيَفِ قَدِّ
አካለ ለስላሳው ከሆነው እጅ
ማራኪና ቀጭን ቁመና ካለው
تَارَةً يُنْشِدُ خُذْ كَاسِي
وَطَوْراً هَاكَ خَدِّي
አንዴ “ጽዋዬን ውሰድ” ይላል
ሌላ ጊዜ “ጉንጬ ይሄው” ይላል
إِنْ أَقُلْ يَا أَلْفَ مَوْلَى
قَالَ لِي يَا أَلْفَ عَبْدِي
“ሺህ ጊዜ ጌታዬ” ብለው
“ሺህ ጊዜ ባሪያዬ” ሲል ይመልሳል
أَوْ سَقَى الْمَمْزُوجَ غَيْرِي
خَصَّنِي بالْصِّرْفِ وَحْدِي
ለሌሎች ቅልቅሉን ቢያጠጣ
ለእኔ ግን ንጹሁን ለብቻዬ መረጠኝ
في هَوَاهُ دَعْ مَلاَمِي
وَاطْرِحْ غَييِّ وَرُشْدِي
በፍቅሩ ውስጥ ወቀሳህን ተወኝ
ስህተቴንም ሆነ ቅንነቴን እርሳው
نَارُ وَجْدِي في هَوَاهُ
كَنَعِيمِ الْخُلدِ عِنْدِي
በእሱ ፍቅር ውስጥ ያለው የናፍቆት እሳት
ለእኔ እንደ ዘለዓለማዊ የጀነት ጸጋ ነው