مَعَانِي قَدْ بَدَتْ عِنْدِي غَرِيبَهْ
ድንቅ ትርጉሞች ታዩኝ
Am
مَعَانِي قَدْ بَدَتْ عِنْدِي غَرِيبَهْ
وَمَا تُفْضِي إِلِيْهْ بَعْدُ أَغْرَبْ
ግሩም የሆኑ ትርጉሞች በኔ ዘንድ ታዩ
ወደ ፊት የሚያመሩትም ደግሞ ይበልጥ ድንቅ ነው
مِنَحْ مِنْ فَضْلِ مَوْلَانَا عَجِيبَهْ
وَمَاذَا فِي عَطَاهُ لَيْسَ أَعْجَبْ
የጌታችን ችሮታ የሆኑ ስጦታዎች ድንቅ ናቸው
በስጦታው ውስጥስ ምን አለ ድንቅ ያልሆነ?
وَعِيدُ الْصَّبِ أَنْ يَلْقَى حَبِيبَهْ
وَسُبْحَانَ الَّذِي قَرَّبْ وَحَبَّبْ
የወዳጅ በዓል ውድ የሆነውን መገናኘት ነው
አቅርቦ ላስወደደው ጌታ ጥራት ይገባው
مَعِي أَقْوَامْ فِي أَعْلَى كَتِيبَهْ
لَهُمْ أَسْرَارْ لَا تُحْصَى وَتُكْتَبْ
በከፍተኛው ማዕረግ ያሉ ሰዎች ከእኔ ጋር አሉ
የማይቆጠሩና የማይጻፉ ምስጢራት አሏቸው
مَوَاهِبْ عَالِيَةْ مَا هِيْ كَسِيبَهْ
وَإِحْسَانُ الْمُهَيْمِنْ لَيْسَ يُحْسَبْ
እነዚህ ልቅ ስጦታዎች በጥረት የተገኙ አይደሉም
የጠባቂው አምላክ ውለታም አይሰላም
وَمَنْ لُهْ سَابِقَهْ يُدْرِكْ نَصِيبَهْ
مُوَفَّى دُونَ أَنْ يَشْقَى وَيَتْعَبْ
ቀድሞ የተጻፈለት ድርሻ ያለው እድሉን ያገኛል
ሳይደክምና ሳይለፋም ሙሉውን ይረከባል
وَنَفْحَةُ بَاسِطِ الْنَّعْمَى قَرِيبَهْ
تَعَرَّضْ يَا فَتَى مِنْهَا تَقَرَّبْ
የጸጋው ለጋስ የሆነው ጌታ ነፋሻ ጸጋ ቅርብ ነው
ወጣት ሆይ! ወደ እሷ ተጠጋና ተቃረብ
عَسَى الْمَكْلُومْ أَنْ يَلْقَى طَبِيبَهْ
فَيُضْحِي الْعِيْشْ لُهْ أَطْيَبْ وَأَطْيَبْ
የተጎዳው ፈዋሹን ያገኝ ይሆናል
ያኔ ኑሮው እጅግ የጣፈጠ ይሆንለታል
وَصَلَّى اللهُ مَا أَفْهَامٌ نَجِيبَهْ
وَعَتْ قَوْلاً بِمَاءِ الْعَيْنِ يُكْتَبْ
የላቁ አዕምሮዎች በዓይን እንባ የሚጻፉትን
ቃላት እስከተረዱ ድረስ የአላህ ሰላት ይውረድ
عَلَى خَيْرِ الْوَرَى الْهَادِي حَبِيبِهْ
وَآلِهْ وَالَّذِي لِلْطُّهْرِ يَصْحَبْ
በፍጥረታቱ ሁሉ በላጭ መሪና ውድ በሆኑት ላይ
በቤተሰቦቻቸውና በንጽህና በተከተሏቸውም ላይ