ْيَاجَمَالُه
Oh, How Beautiful He Is!
Am
آه يَا جَمَالُه يَا جَمَالُهْ
سِيدْنَا النَّبِى يَا جَمَالُهْ
ኦ! ውበቱ! ውበቱ እንዴት ያምራል!
ኦ! ውበቱ! ውበቱ እንዴት ያምራል!
سِيدْنَا النَّبِى يَا جَمَالُهْ
ጌታችን ነቢዩ ውበታቸው እንዴት ድንቅ ነው!
كَحِيلُ الطَّرْفِ حَبِيبِي لَوْ تَرَاهُ
ضَحُوكُ السِّنِّ لِلْعَاشِقِ رَمَاهُ
ፍቅሬን ብታዩት ዓይኑ የኩለ ነው
በፈገግታውም አፍቃሪውን በመገረም ጣለው
بَهِيُّ الطَّلْعَةْ فَالْمَوْلَى اصْطَفَاهُ
وَكُلُّ الْخَلْقِ أَنَارَ بِنُورِ طه
ፊቱ የሚያበራ ነውና ጌታ መረጠው
ፍጥረትም ሁሉ በጣሀ ብርሃን በራ
وَلَا ظِلُّ لَهُ بَلْ كَانَ نُوْرَا
تَنَالَ الشَّمْسُ مِنْهُ هُوَ الْبُدُوْرَ
ጥላ አልነበረውም ይልቁንም እርሱ ብርሃን ነውና
ፀሐይ ከርሱ ፀዳልን ወሰደች እርሱ ሙሉ ጨረቃ ነውና
وَلَمْ يَكُنِ الْهُدَى لَوْلَاهُ ظُهُوْرَا
وَ كُلُّ الْكَوْنِ أَنَارَ بِنُوْرِ طَــــــهَ
እርሱ ባይኖር ኖሮ ቅኑ መንገድ ባልታየ
መላው ዓለምም በጣሀ ብርሃን በራ
وَكَفُّ الْمُصْطَفَى كَالْوَرْدِ نَادِى
وَعِطْرُهَا يَبْقَى إِذَا مَسَّتْ أَيَادِى
የሙስጠፋ እጅ እንደ ረጠበ ጽጌረዳ ነው
የነኩትም እጆች መዓዛው አይለያቸው
وَعَمَّ نَوَالُهَا كُلَّ الْعِبَادِ
حَبِيبُ اللهِ يَا خَيْرَ الْبَرَايَا
ችሮታው ለባሮቹ ሁሉ ደረሰ
የአላህ ወዳጅ ሆይ የፍጥረት ሁሉ በላጭ
وَرِيقُ الْمُصْطَفَى يَشْفِي الْعَلِيلَ
وَعَيْنُ قَتَادَةَ خُذْهَا دَلِيلًا
የሙስጠፋ ምራቅ ህመምተኛን ይፈውሳል
የቀታዳህን ዓይን ለዚህ ማስረጃ አድርገህ ውሰድ
تَفَلَ فِي الْبِئْرِ أَضْحَتْ سَلْسَبِيلًا
وَصَارَ لِصَحْبِهِ شَهْدًا مُدَامًا
በጉድጓዱ ቢተፉ ምንጭ ሆኖ ፈሰሰ
ለባልደረቦቹም እንደ ማር የሚጣፍጥ ሆነ