بَادِرْ لَقَدْ فَاتَتْكَ الْغَنَائِمْ
ፍጠን! ምርኮዎቹ አምልጠውሃል
Am
Am
بَادِرْ لَقَدْ فَاتَتْكَ الْغَنَائِمْ
تَقَاسَمُوهَا وَأَنْتَ نَائِمْ
ፈጥነህ ተነሳ! በእርግጥ ምርኮዎቹ አምልጠውሃል
አንተ ተኝተህ ሳለህ ተከፋፍለዋቸዋል
وَلَوْ رَأَيْتَ الَّذِينَ فَازُوا
نُحْتَ كَمَا نَاحَتِ الْحَمَائِمْ
ያሸነፉትን አይተህ ቢሆን ኖሮ
እርግቦች እንደሚያለቅሱት አንተም ባለቀስክ ነበር
إِنْ رُمْتَ أَلَّا تَكُونَ نَادِمْ
قُمْ لِحَبِيبِ الْقُلُوبِ لَازِمْ
ጸጸተኛ መሆንን ካልፈለግህ
ተነሳና የልቦችን ተወዳጅ ሙጥኝ በል
وَلَازِمِ الْبَابَ يَا مُعْنَّى
إِنَّ الْسَّعِيدَ الَّذِي يُلَازِمْ
አንተ የደከምክ ነፍስ ሆይ! ደጃፉን ሙጥኝ በል
የታደለ ማለት በደጃፉ የሚዘወትር ነውና
مَنْ لَازِمَ الْبَابَ نَالَ قُرْبا
وَفَازَ بِالْأَجْرِ وَالْغَنَائِمْ
ደጃፉን ሙጥኝ ያለ መቃረብን አገኘ
በምንዳና በምርኮም ተሳካለት
وَلَا تَنَمْ سَاعَةَ الْتَّجَلِّي
فَلَيْسَ يَحْظَى بِالْأَجْرِ نَائِمْ
መለኮታዊ መገለጥ በሚሆንበት ሰዓት አትተኛ
ተኝቶ ያለ ሰው ምንዳን ሊያገኝ አይችልምና
قَدْ جَرَحَتْ قَلْبِيَ الْخَطَايَا
وَلَسْتُ أَلْقَى لَهَا مَرَاهِمْ
ኃጢአቶች ልቤን ክፉኛ አቁስለውታል
ለእርሱም ምንም ዓይነት ፈውስ አላገኘሁም
سِوَى الْرِّضَا مِنْكَ يَا إِلَهِي
يَا وَاسِعَ الْجُودِ وَالْمَكَارِمْ
ጌታዬ ሆይ! ካንተ ውዴታ በቀር
አንተ ችሮታህና ልግስናህ ሰፊ የሆንክ
وَقَدْ تَوَسَّلْنَا يَا إِلَهِي
بِسَيِّدِ الْعَرَبِ وَالْأَعَاجِمْ
ጌታችን ሆይ! ወደ አንተ ተቃርበናል
በዓረቦችና በዓረብ ባልሆኑትም ሁሉ መሪ በሆኑት
نَبِيِّنَا الْمُصْطَفَى الْتِّهَامِي
مَنْ جَاءَ لِلْأَنْبِيَاءِ خَاتَمْ
በነቢያችን በሙስጦፋ በቲሃሚው
ለነቢያት ሁሉ መደምደሚያ በሆኑት