لِغَيْرِ جَمَالِكُمْ نَظَرِي حَرَامُ
ከውበትዎ ሌላ እይታዬ እርም ነው።
Am
لِغَيْرِ جَمَالِكُمْ نَظَرِي حَرَامُ
وَغَيْرُ كَلَامُكُمْ عِنْدِي كِلَامُ
ከእናንተ ውበት ውጭ ማየት ለእኔ እርም ነው
ከንግግራችሁ ሌላ ንግግር ለእኔ ከንቱ ነው።
وَعُمْرُ الْنَّسْرِ مِنْكُمْ بَعْضُ يَوْمٍ
وَسَاعَةُ غَيْرِكُمْ عَامٌ فَعَامُ
ከእናንተ ጋር የንስር ዕድሜ እንደ ቀን ከፊል ነው
ከሌሎች ጋር ያለ አንዲት ሰዓት ግን ዓመታት ነው።
وَصَبْرِي عَنْكُمُ شَيْءٌ مُحَالٌ
وَمَا لِي قَاتِلٌ إِلَّا الْفِطَامُ
ከእናንተ መለየትን መታገስ የማይቻል ነገር ነው
መለየት (ፍጣም) እንጂ እኔን የሚገድለኝ የለም።
إِذَا عَايَنْتُكُمْ زَالَتْ هُمُومِيْ
وَإِنْ غِبْتُمْ دَنَا مِنِّيْ الْحِمَامُ
ባየኋችሁ ጊዜ ጭንቀቶቼ ይወገዳሉ
ከራቃችሁኝ ግን ሞት ወደ እኔ ይቀርባል።
أَوَدُّ بِأَنْ أَكُونَ لَكُمْ جَلِيسًا
وَتُنْصَبَ لِي بِرَبْعِكُمُ خِيَامُ
የእናንተ አጋር መሆንን እመኛለሁ
በሰፈራችሁም ድንኳኖቼ እንዲተከሉልኝ እሻለሁ።
فَدَاوُوا بِالْوِصَالِ مَرِيضَ هَجْرٍ
يَهِيمُ بِكُمْ إِذَا سَجَعَ الْحَمَامُ
በመለየት የታመመውን በመገናኘት ፈውሱት
እርግቦች ባዜሙ ቁጥር በእናንተ ፍቅር የሚቃትተውን።
حَدِيثُ غَرَامِهِ فِيكُمْ قَدِيمٌ
وَمَلْبَسُهُ مِنَ الْحُبِّ الْسِّقَامُ
የእርሱ የእናንተ ፍቅር ታሪክ ጥንታዊ ነው
ከፍቅሩ የተነሳ የለበሰው ልብስ ህመም ነው።
فَأَنْتُمْ فِي الْأُصُولِ أَجَلُّ أَصْلٍ
إِذَا شِئْتُمْ تَحَصَّلَ لِي الْمَرَامُ
እናንተ በመሰረቶች ሁሉ የላቃችሁ መሰረት ናችሁ
እናንተ ከፈቀዳችሁ ምኞቴ ሁሉ ይሳካል።
بِكُمْ صَعْبُ الْأُمُورِ يَعُودُ سَهْلًا
فَبِالْإِحْسَانِ جُودُوا يَا كِرَامُ
በእናንተ አስቸጋሪ ነገሮች ሁሉ ቀላል ይሆናሉ
እናንተ ቸሮች ሆይ! በበጎነት ልግስናችሁን ስጡኝ።
وَلَيْسَ سِوَاكُمُ لِلْجُودِ أَهْلًا
فَكَيْفَ نَزِيلُ سُوحِكُمُ يُضَامُ
ከእናንተ ሌላ ለልግስና የሚገባው የለም
ታዲያ በደጃችሁ ያረፈ እንግዳ እንዴት ይበደላል?